ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

“በምንፈልገው መንገድ ይህን ውጤት ከጥሩ ጨዋታ ጋር ማሸነፍ ስለቻልን በጣም ደስ ብሎኛል ” -ፍሬው ጌታሁን

የ20ኛው ሳምንት የዛሬ ምሽቱ ድሬዳዋ ከተማ ከሲዳማ ቡና ባደረጉት ጨዋታ የድሬደዋ ከተማው ግብ ጠባቂ ፍሬው ጌታሁን በሱፐር ስፖርት ቴክኒካል ቲም የምሽቱ ጨዋታ ኮከብ ተብሏል። ከጨዋታው በኋላ ፍሬው በሱፐር ስፓርት ጋር ቆይታም አድርጓል።
ስለ ዛሬው ጨዋታው ?
” በርግጥ እንበቀላለን እያልን ነበር ከልጆቹ ጋር ። እንፈልገው ነበር ይህን ውጤት በምንፈልገው መንገድ  ይህን ውጤት  ስላገኘነው እና ከጥሩ ጨዋታ ጋር ማሸነፍ ስለቻልን በጣም ደስ ብሎኛል፤ እንፈልገውም ነበር ፣ ስላገኘነውም ደስ ብሎኛል። “
የዛሬው ሦስት ነጥብ ማግኘት ለቡድኑ የሚሰጠው ትርጉም ?
” ሁለታችንም ነጥባችን አነስተኛ ከመሆኑ አንፃር ሁለታችንም ላለመውረድ ነው የምንሰራው። ሁለታችን በተገናኘን ሰአት አንዳችን የግዴታ ነጥብ መያዝ አለብን። ያንን ደግሞ እኛ ተነጋግረን መጥተን አሳክተናል ፣ በጣም ደስ ብሎናል።
ብዙ ኳሶች አድነሃል ፤ ካዳንከው በኃላ ደስ ያለህ የትኛው ነው ?
“በመጨረሻ አካባቢ የመለስኳት በጣም ደስ ብላኛለች”
የቡድኑ የዘንድሮ ዕቅድ ?
” ዘንድሮ ሰውየውም የራሱን ለማስተካከል ብዙም ዕቅድ አልነበረውም። አሁን ላይ ያንን ነገር እያስተካከለ ነው። ዘንድሮ ሳንወርድ የሚቀጥለው ዓመት በራሱ የተሻለ ነገር ለመስራት ተዘጋጅናል”
የሱፐር ስፓርት ቴክኒካል ቲም የጨዋታው ኮከብ ተብለሃል እንኳን ደስ ያለህ
” እሺ አመሠግናለሁ ‘