አትሌቲክስ

#በመጀመሪያው ቀን ኢትዮጵያዊያን አትሌቶች ድል ተቀዳጅተዋል

    From Abdu Muhammed
በዛምቢያ ንዶላ በሚካሄደው የአፍሪካ ከ20 እና ከ18 ዓመት በታች አትሌቲክስ ሻምፒዮና ለመሳተፍ የተጓዘው እና በትላንትናው እለት መጉላላት አጋጥሟቸው የነበሩት የኢትዮጵያ አትሌቲክስ የታዳጊዎችና የወጣቶች ቡድን በመጀመሪያ ቀን ድል ቀንቶታል
በውጤቱም
በ3,000 ሜ ሴቶች ከ20 አመት በታች ከ1ኛ እስከ 3ኛ ያለውን ደረጃ በመያዝ ሜዳልያውን ጠራርገውታል።
🇪🇹 አስማረች አንለይ 1ኛ ሆና ወርቅ፣
🇪🇹 የኔዋ ንብረት 2ኛ ሆና ብር፣
🇪🇹 አይናዲስ መብራቱ 3ኛ ሆና ነሃስ ሜዳልያ አግኝታለች።
#ከ18 አመት በታች 1500 ሜ ሴቶች
#አሰለፍ አማረ 3ኛ ሆና የነሃስ ሜዳልያ ስትሸለም
በዚሁ ርቀት በተመሳሳይ እድሜ በወንዶች
ፈይሳ ኢያሱ 6ኛ ደረጃን ይዞ አጠናቋል።