ዜናዎች

# በሊጉ ጅማሮ ውጤታማ መሆን ያልቻለው ሲዳማ ቡና አዲስ አሰልጣኝ ነገ ይፋ ያደርጋል !

በ2014 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጠንካራ ተፎካካሪ በመሆን በሶስተኛ ደረጃ ማጠናቀቅ የቻለው ሲዳማ ቡና በዘንድሮው የውድድር አመት አስከፊ የሚባል አጀማመር ላይ ይገኛል።
በዘንድሮ የዝዉዉር መስኮት ከፍተኛ እንቅስቃሴ በማድረግ አዳዲስ ተጫዋችን ማስፈረም የቻለው ሲዳማ ቡና በአንፃሩ እስካሁን ባደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ከድሬደዋ ከተማ 2 ለ 2 ፣ በሀድያ ሆሳዕና 4 ለ1 እንዲሁም በፈረሰኞቹ አስከፊ በሆነ የ5 ለ 1 ሽንፈት በማስተናገድ ማግኘት ከነበረበት 9 ነጥብ ማግኘት የቻለው 1 ነጥብ ብቻ ነዉ። በተጨማሪ አራት አስቆጥሮ 11 ጎሎች በማስተናገዱ ይታወቃል ። በውጤቱም የተነሳ ቦርዱ አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመን ወደ ሀዋሳ በመጥራት ከክለቡ ኃላፊነት አሰናብተዋል።
እንደሚታወሰው አሰልጣኝ ወንድማገኝ ተሾመ ክለቡን በረዳት አሰልጣኝነት ሲመሩ የነበረ ሲሆን በክረምቱ ላይ ዕድገት አግኝተው ወደ ዋና አሰልጣኝነት የተረከቡ ቢሆንም በውጤቱ ማጣት ቦርዱ በማሰናበት በአስቸኳይ አዲስ አሰልጣኝ ለመቅጠር እየተንቀሳቀሱ ይገኛል።
በሚወጡ የተለያዩ መረጃዎች  ሦስት አሰልጣኞች በዕጩነት ቀርበዋል። በደጋፊዎች ፍላጎት በ2013 የውድድደር ዓመት ፋሲል ከነማን ለመጀመሪያ ጊዜ ለኢትዮጵያ ቤትኪንግ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮንት ያበቁት ውጤታማ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ለክለቡ መፍትሔ መሆን እንደሚችሉ ደጋፊዎች እየተናገሩ ይገኛል ። በተጨማሪም አሠልጣኝ ዻውሎስ ጌታቸው ( ማንጎ ) አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው  በዕጩነት ቀርበዋል። ይሁንና በቦርዱ አካባቢ ያሉ ለክለቡ ውጤት ከመጨነቅ ይልቅ ግላዊ ጥቅም ያተኮሮ ሰዎች የተለያዩ የሐሳብ ልዩነቶችን በማቅረብ በግላዊ ቅርበት እነሱ የፈለጉትን የአሰልጣኝ ቅጥር ለማሳካት እየተሯሯጡ እንደሆነ ተሠመቷል። የአሰልጣኝ ቅጥሩን በተመለከተ ክለቡ ነገ ይፋ ያደርጋል ተብሎ ይጠበቃል።