ዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ ከረጅም ዓመታት በኋላ ለኢትዮጵያውያን አሰልጣኞች እድል ሊሰጥ መሆኑ ተሠማ !

አንጋፋው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ ለረጅም ዓመታት እና በተለያዩ ዘመናት የውጭ አገር አልያም የአውሮፓውያን አሰልጣኞችን በመቅጠር ከሀገር ውስጥ ክለቦች ለየት ያደርገዋል፡፡

በክለቡ ታሪክ ከ19 ዓመት በላይ የውጭ ሀገር አሰልጣኞች እንደሳለጠኑት ሲታወቅ ቅዱስ ጊዮርጊስን ለመጀመርያ ጊዜ ያሰለጠኑት አውሮፓዊ አሰልጣኝ ጀርመናዊው ፒተር ሽንግተር በ1967 ዓ.ም ሲሆኑ ፡ፒተር ከቅዱስ ጊዮርጊስ ሃላፊነታቸው በኃላ በ1968ዓ.ም ተዘጋጅቶ በነበረው 10ኛው የአፍሪካ ዋንጫ የዋልያዎቹ አሰልጣኝ ለመሆን ችለዋል ።

 

የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ የፕሪሚየር ሊጉን ዋንጫ በተደጋጋሚ በማሸነፍ ቀዳሚ ሲሆን በተመሣሣይ ቅዱስ ጊዮርጊስ በተከታታይ ዓመታት የውጭ ሀገር አሰልጣኞች በመሰልጠንም ከሌሎች የሀገር ውስጥ ክለብች ቀዳሚ ያደርገዋል።
ጥቂቶቶቹን የውጭ አሰልጣኞች ለማስታወስ በቅርቡ ክለቡ የ63 ዓመቱ ሰርቢያዊው አሰልጣኝ ዝላትኮ ክራምፖቲክ ጨምሮ 4 ሰርቢያውያን ፣ 3 ጀርመናውያን፣ 2 ሆላንዳያዊያን ፣ 2 ጣሊያናዊያን ከዚህ በተጨማሪም ከፖርቹጋል ፣ ሶኮትሽ ፣ደቡብ አፍሪካ እና ከሌሎችም ሀገር የመጡ አሰልጣኞች ለአጭር ጊዜ በማሰልጠን ክለቡን ለየት ያደረገዋል።

ይሁንና የታማኝ ምንጮች መረጃ እንደሚጠቁመው ከሆነ ላለፉት አራት ዓመታት ከፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ የራቀው የቅዱስ ጊዮርጊስ ስፖርት ክለብ በቀጣይ ኢትዮጵያዊ በዋና አሰልጣኝነት ለመቅጠር መታሰቡ ተሰምቷል።

እንደመረጃው ከሆነ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የወቅቱ አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ከአፍሪካ ዋንጫ በኃላ የቅዱስ ጊዮርጊስ ዋና አሰልጣኝ እንደሚሆኑ ተናግሯል።