አፍሪካ ዜናዎች

ቅዱስ ጊዮርጊስ በሴካፋ ሻምፒዪና የዮጋንዳ ግብ ጠባቂ የነበረውን ቻርልስ ሊያስፈርም ነው !

ዮጋንዳዊው ግብ ጠባቂ ቻርልስ ሉክዋጎ ለቅዱስ ጊዮርጊስ ሊፈርም መሆኑ ተዘገበ። ለዮጋንዳው KCCA FC በግብ ጠባቂነት እየተጫወተ የሚገኘው የ26 ዓመቱ ቻርለስ ሉክዋጎ በኢትዮጵያ እየተካሄደ ባለው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች ሻምፒዮና ላይ የዮጋንዳ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን ግብ ጠባቂ በመሆን በኢትዮጵያ ይገኛል።
መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ግብ ጠባቂው ቻርየልስ ሉክዋጎ እየተካሄደ ባለው የሴካፋ ከ 23 ዓመት በታች ውድድር ላይ ለዮጋንዳ ተሰልፎ ተጫውቷል። ዮጋንዳ ኤርትራን ባሸነፈችበት እና በ5ኛነት ባጠናቀቀችበት የትላንቱ ጨዋታ ተሰልፎ የተጫወተው ሲሆን አሁን የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብን ለመቀላቀል ስምምነት መድረሳቸው ታውቋል። ኬኒያዊውን ሮበርት ማታሲን በመኪና አደጋ እና የስምምነት ውሉ መጠናቀቁን ተከትሎ የተለያየው የቅዱስ ጊዮርጊስ ክለብ ዮጋንዳዊውን ቻርለስ ሉክዋጎ ያስፈርማል ተብሎ ይጠበቃል