
መስፍን ከቅርብ ሳምንታት በጉዳት መልስ በቤትኪንግ ላይ ያለተሰለፈ ይገኛል። የቤትኪንግ በቀጣይ አዘጋጅ ሐዋሳ ከተማ ከመሆኗ አንፃር ለሐዋሳ ምን ይጠቅማል በሚል ከመስፍን ጋር ኢትዮኪክ ቆይታ አድርገናል።
ኢትዮኪክ:- ከጉዳት መልስ እንዴት ነህ?
መስፍን:- ከጉዳት መልስ አሪፍ ነኝ። ትንሽ በርግጥ ከበድ ይላል። ግን በስራ ይመጣል።
ኢትዮኪክ:- በድሬዳዋ ቡድናችሁ የተሻለ ነበር ማለት ይቻላል ? ምን የተለየ ነገር ነበር?
መስፍን:- አዎ ! በጣም የሚያስፈልገንን ውጤት ይዘናል ብዬ አስባለሁ ። ቡድኔም ጥሩ መሻሻል አሳይቷል። ይህን ደግሞ ማስቀጠል አለብን ብዬ አስባለሁ።
ኢትዮኪክ:- የቡድናቹ ጠንካራ ጎን ?
መስፍን:- የቡድናችን ጠንካራ ጎን የምለው ህብረታችን ነው። ይህን ህብረታችንን ደግሞ ማስቀጠል አለብን እላለሁ።
ኢትዮኪክ:- ዘንድሮ ለቡድንህ የምፈልገውን አድርጊያለሁ ብለህ ታስባለህ?
መስፍን:- በትንሽ አዎ። ግን ከዚህ በላይ ይጠበቅብኝ ነበረ።
ኢትዮኪክ:- ቀጣይ ሳምንት ቤት ኪንግ በሃዋሳ ከተማ ይደረጋል ፣ የሚጠቅማችሁ ነገር ይኖራል ?
መስፍን:- አዎ በቀጣይ ቤትኪንግ በሐዋሳ በሜዳችን በመሆኑ ይጠቅመናል። በጣም አሪፍ አጋጣሚ ነው ። ከእኛ የሚያስፈልገው አሁን ያለንን ህብረት በሜዳችንም ላይ ማስቀጠል የሚያስፈልገው።
ኢትዮኪክ:- የቤትኪንግ ውድድር ስንተኛ ሆነን እናጠናቅቃለን ትላለህ?
መስፍን:- እግዚአብሔር ፍቃዱ ከሆነ ከሁለተኛ እስከ አራተኛ እናጠናቅቃለን እላለሁ።ፈጣሪ ካለ ደግሞ የአፍሪካ መድረክ መካፈል ።
