ዜናዎች

” ሀገሬን በየትኛውም የውድድር መድረክ መወከል በመቻሌ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል “- ሽመልስ በቀለ

ሽመልስ በቀለ -ምስር ኤል ማካሳ
በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ለተከታታይ አመታት ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ የሚገኘው እና በተለየ መልኩ በዘንድሮው የግብፅ ሊግ በግሉ የተሳካ ጊዜን በማሳለፍ የሚገኘው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን የአማካይ ሽመልስ በቀለ  ቡድኑ አሸንፎ የወጣበት ወሳኝ ጎል አስቆጥሯል። በግብፅ ፕሪምየር ሊግ በትላንትናው የ21ኛ ሳምንት ጨዋታ የሽመልስ ምስር ኤል ማካሳ የቀድሞ የጋቶች ፓኖም ክለብ የሆነውን አል ጎናን በሜዳው አስተናግዶ በ90ኛው ደቂቃ ሽመልስ ባስቆጠረው ብቸኛ ጎል ምስር ኤል ማሰካስ አሸንፎ ሶስት ነጥብ ይዞ ወጥተዋል።
በኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ብቸኛው በውጪ ሊግ የሚጫወተው ሽመልስ በቀለ በዘንድሮው የግብፅ ፕሪምየር ሊግ በ 7 ጎሎች ከከፍተኛ ጎል አስቆጣሪው ከ 11 ጎሎች ከሚመራው  በ4 ጎሎች ርቆ እንዲም  ከዋናው  በታች ካሉት ሊሎች   የከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎችት  የስም ዝርዝር ውስጥ ሽመልስ ይገኛል።
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ድንቅ የአማካይ እና በዘንድሮው የአፍሪካ ዋንጫ ለሁለተኛ ጊዜ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድንን በሁለተኛ አምበልነት ለአፍሪካ ዋንጫ ካሳለፉት የዋልያዎቹ አባላት አንዱ ሽመልስ በቀለ በትላንት ልዪ የሽልማት  ዝግጁት ከጀማል ና ከጌታነህ ጋር የተበረከተለት ልዮ ሽልማትን አስመልክቶ የተሰማውን ደስታ በተመለከተ በዚህ መልኩ ገልፆልናል” ሀገሬን በየትኛውም የውድድር መድረክ መወከል በመቻሌ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል። በትላንትናው ዕለት ለተደረገልኝ ሽልማት ከልብ አመሰግናለሁ። በዚህ አጋጣሚ እዚህ ደረጃ እንድደረስ ትልቅ ዕርዳታ ላደረጉልኝ የብሔራዊ ቡድኑ የተለያዩ አካላት ማመስገን እፈልጋለሁ ” በማለት ደስታውን ገልጿል

One thought on “” ሀገሬን በየትኛውም የውድድር መድረክ መወከል በመቻሌ ከፍተኛ ኩራት ይሰማኛል “- ሽመልስ በቀለ

Comments are closed.