ናይጄሪያዊው ኦኪኪ አፎላቢ በ2010 ዓ.ም ጅማ አባ ጅፋር የፕሪምየር ሊጉ ዋንጫ ሲያነሳ በ23 ጎሎች የሊጉ ኮከብ ግብ አስቆጣሪም በመሆን ይታወሳል። ተጨዋቹ በጅማ አባጅፋር ክለብ ከመጀመሪያው ስኬቱ በኃላ ወደ ግብፅ በማምራት ለግብፁ ኢስማዒልያ ኤስ ሲ ጋር ቢ ያልተሳካን ጊዜ አሳልፎ ወደ ጅማ አባጅፋር ቢመለሰም በዝውውር ሂደቱ ወቅት ለፊርማ በማስመሰል ወንጀል ጥፋተኛ ሆኖ በመገኘቱ 6 ወር ዕገዳና 25 ሺህ ብር ቅጣት ተላልፎበትም ነበር።
ናይጄሪያዊው ኦኪኪ አፎላቢ በኃላም ወደ መቐለ 70 እንደርታ በማምራት የ2012 ዓ.ም የፊት መስመሩን በ14 ጨዋታዎች 10 ጎሎችን አስቆጥሯል። መቐለ 70 እንደርታ ዘንድሮ በቤትኪንግ አለመወዳደሩን ተከትሎ ኦኪኪ አፎላቢ የቀድሞ አሰልጣኙ ገብረ መድህን ሀይሌን ተከትሎ በቅርቡ በሲዳማ ቡና መፈረሙ ይታወሳል። በ17ኛው ሳምንት ኦኪኪ በሲዳማ ቡድና ማሊያም የ2013 የቤትኪንግ ፕሪምየር ሊግ የመጀመሪያ ጎሉንም አስቆጥሯል። ኢትዮ ኪክ ክናይጄሪያዊው ኦኪኪ አፎላቢ ያደረግነውን ቆይታ ታነቡት ዘንድ እንሆ :-
ኢትዮ ኪክ:- -በኢትዮጵያ ሊግ ውስጥ መጫወትን እንዴት ነው የምትገልፀው ?
ኦኪኪ :- በናይጄሪያ ሊግ ውስጥ ያለኝ ብቃት በፕሮፌሽናል ተጫዋችነቴ ደረጃ ለማሳየት አንድ ወይም ሁለት ማሳየት ያስፈልገኛል። ግን እዚህ በፕሮፌሽናል ተጫዋች ነው ብለው ሰዎችን ላማሳመን የበለጠ ጥረት ማድረግ አለብኝ። እንደምታውቂው እንደመጣሁ የመጀመሪያ የውድድር አመቴ ላይ ከፍተኛ ግቦችን በኢትዮጵያ ሊግ በማስቆጠር የመጀመሪያው የውጭ ተጨዋች ነኝ። በርግጥ በመጀመሪያው ዓመት ላይ ብዙ ነገሮችን በኢትዮጵያ አጋጥሞኛል ። እግዚአብሔርን አመሠግናለሁ ምክያቱም ከጉዳት መልስ ነበር እንደዛ ጥሩ ብቃት ላይ የነበርኩት።
ኢትዮ ኪክ:- – ለሶስት ዓመት በኢትዮጵያ ሊግ ቆይተሃል ፤ ኢትዮጵያን እንዴት ትገልፃታለህ ?
ኦኪኪ:- አትዮዽያ በጣም አድርጌ ነው የምወዳት። አንዳንድ ሰዎች አሁንም ሰዎች በረሃብ እንደሚሞቱ የሚኒገሩ አሉ።
በኢትዮጵያ ለሎችም መጠለያ እና ስደተኞችን የምታስተናግድ አፍሪካዊት ሀገር መሆኗን የተገነዘቡ ጥቂት ሰዎች ናቸው ። ለምሳሌ ወደ 730 000 የሚሆኑት ስደተኞች በዋናነት ከሶማሊያ ፣ ከሱዳን ፣ ከደቡብ ሱዳን ፣ ከኤርትራ እና ከኬንያ ተመዝግበዋል ፡፡ ይህንን ያልተረዱ ሰዎች አሉ። ጄኔቫ UNDP ከሠራሁ በኋላ አዲስ አበባ ከሚገኘው ቢሮ ውስጥ ተቀላቀልኩ ፤ ሰዎች ብዙውን ጊዜ በኢትዮጵያ ውስጥ ከምግብ ዋስትና ጋር ችግሮችን የሚናገሯቸው የግንዛቤ ችግሮች እንዳሉ ሆነው። በርግጥ በአሁኑ ወቅት ሀገሪቱ እየገገጠማት ያለውን ቀውስ ሁኔታ ችላ ማለት አይቻልም ፡፡
ኢትዮ ኪክ:- -የኢትዮጵያን የሊግ ደረጃ እንዴት ነው የምትለካው ?
ኦኪኪ : – እኔ ምለካው እንግዲህ በአሥራ ስድስቱ ወይም አሁን ባሉት በአስራ ሶስቱ ክለቦች ተወዳዳሪ ክለቦች መካከል ያለው ጥንካሬን ፣ የሊጉ የአሰራር ሂደት ፣ክለቦቹ ከሌሎቹ አንፃራዊ ያላቸው እውቅና እንዲሁም የከፍተኛ ዲቪዚዮን በሌሎቹም የታችኛው ሊጎች ጋር ያለው ጥምረት እና እግርኳሱን የማስተዋወቁ አሰራርን እና ህጎች ያካትታል።አሁን ትልቁ። DSTV ወደ ኢትዮጵያ መጥቷል። በጣም ደስተኛም ነኝ። ይሄ የኢትዮጵያን ሊግ ለማስተዋወቅ ትልቅ በመንገድም ነው።
ኢትዮ ኪክ:- – በኢትዮጵያ ሊግ በመጫወትህ በሀገርህ ከፕሮፌሽናል ተጨዋቾች አንፃር የሚሰጥህ ቦታ ?
ኦኪኪ : – አዎ ቦታ አለው ። በርግጥ ንፅፅሩ የራሱ ልዩነቶች ቢኖረውም። በኢትዮዽያ ሊግ በመጫወቴ የሚሰጠኝ ቦታ እንዳለ ሆኖ ግን ሁሉም ተጨዋቾች የተሻለ ክለብ መፈለግ አይቅረም ። ስለዚህ ትልቅ ክበብ በማምራት ወደ ፊት የተሻለ አስባለሁ። በዚህ አጋጣሚ ኢትዮጵያን ሊግ እወዳለሁ።
ኢትዮ ኪክ:- – በኢትዮጵያ ሊግ መጫወት ለውጭ ተጨዋቾች ክፍያውስ ከሌሎች አንፃር ?
ኦኪኪ : – ክፍያው በተመለከተ አንድ ሰው ስራ ሰርቶ እንደሚያገኘው ለሰራበት አገልግሎት ወይም በሙያው እንደሚከፈለው ደመወዝ የሚከፍለው ዋጋ ነው። ክፍያዎች ምናልባት ተያያዥ ወጪዎችንም ያካትታሉ። በቁጥር ባላስቀምጥም በተለምዶ አንድን ነገር ከሌላው እንደምናወዳድረው ሁሉ ክፍያውንም የሌሎችን ማወዳደሩ ጥሩ ነገር ሆኖ ባይታየኝም። ራሳችንን ከሌሎች ጋር ማወዳደሩ ለሌሎች በባህሪያችን እንዲነዱ ያስችላቸዋል። ይህ ዓይነቱ ንፅፅር በአንቺ እና በሌላ ሰው መካከል እንደማለት ነውና ፡፡ አንዳንድ ጊዜ ይህን ብሎ ማለት ከፍ ያለ ክፍያም እንደመፈለግ ስለሚሆን እና ሌላኛው ሰው ማድረግ እንደልቻለ የመፈለግ ስለሚሆን ይህን በዚህ መልኩ ነው የምገልጸው።
ኢትዮ ኪክ:- -በአዲሱ ክለብህ ሲዳማ ቡና ደስተኛ ነህ ?
ኦኪኪ : – አዎ ። ወደ ሲዳማ ቡና በመምጣቴ እና በአዲሱ ክለቤን በመቀላቀሌ ደስተኛ ነኝ። በቀጣይ ጨዋታዎች ሲዳማ ቡናን ወደ ተሻለ ደረጃ ለማሳደግ ነው ፍላጎቴ። ምክንያቱም የፈረምከት የስድስት ወር ኮንትራት ነውና ። የተሻለ ደረጃ እራሴን ማድረስም እፈልጋለሁ ፡፡
ኢትዮ ኪክ:- -በኢትዮጵያ ሊግ የውጭ ለተጫዋቾች ጥሩ ነገሮች / ችግሮች ምንድናቸው?
ኦኪኪ:- የኢትዮጵያ ኢኮኖሚ በአፍሪካ ውስጥ በጣም ከፍተኛ ደረጃ ከተቀመጡ ሀገራት መካከል አንዱ ነው። በህዝብ ቁጥርም ከአገሬ ናይጄሪያ ቀጥላ ሁለተኛ ናት።
ስለዚህ የውጭ ተጫዋቾችን በኢትዮጵያም እንዲሰሩ ማድረግ በጥሩ ነገር ይመስለኛል ፡፡ ችግሮች ብዬ የምለው ደግሞ የሰዎች የግንዛቤ ችግር አለ ።
ኢትዮ ኪክ:- – አንተ በግለህ የውጭ ተጨዋች በመሆንህ የገጠመህ ችግር ይኖራል ?
ኦኪኪ:- አዎ። ብዙ ጊዜ ገጥሞኛል ያውቃል። ግን ክብሩ ይስፋ ለሃያሉ አምላክ ተወጥችኃለሁ። እንዳልኩሽ በኢትዮጵያ ሊግ ውስጥ ከጅማ አባ ጅፋር የማይረሳ ታሪክ አለኝ። በኢትዮዽያ ሊግ በመጀመሪያ የውድድር ዘመኔ የመጀመሪያው 23 ጎሎችን አስቆጥራለሁ ፡፡ ይሄ ትልቅ ታሪክ ነው።
ኢትዮኪክ:– አሁን ላይ ኦኪኪ አማሪኛ ይናገራል ?
ኦኪኪ :- አማርኛ ለመስማት / መረዳት ስድስት ወር ፈጅቶብኛሌ ። አማርኛ በጣም የምወደው ቋንቋ ነው። እናም አማርኛ የሚናገረው ኢትዮጵያ ብቻ አይደለችም እኛም መናገር ጀምረናል ልልሽ ነው
ኢትዮኪክ:– ስለቃለመጠይቁ አመሠግናለሁ
ኦኪኪ :- እኔም በጣም አድርጌ አመሠግናለሁ።