አትሌቲክስ ዜናዎች

– ምድብ ሁለት አትሌት ጌትነት ዋለ

አትሌት ጌትነት ዋለ በቶኪዮ በኦሎምፒክ ለኢትዮጵያ ሜዳሊያ ከሚጠበቁ አትሌቶች አንዱ ነው። አትሌቱ ሩጫን በልጅነቱ 4 ኪ.ሜ ወደ ትምህርት ቤቱ በመሮጥ የጀመረው አሁን ላይ በኦሎምፒክ መድረክ በውጤት ከሚጠበቁ አንዱ አትሌቶች አንዱ ነው። አትሌቱ በ13 ዓመቱ ወደ ሩጫው ዓለም እንደገባ ሲነገር
በወቅቱ በ 1500 ሜትር እና በ 3000 ሜትር ርቀቶች በክልል ሻምፒዮና ላይ ያሳየው ውጤት አሰልጣኝ ተሾመ ከበደ እይታ ውስጥ በመግባቱ አሰልጣኙ ወደ አዲስ አበባ እንደመጣ አድርገውት አሁን ላይ አትሌቱ ለደረሰበት መንገዱን አመቻቸተዋል።
በዓለም አቀፍ ደረጃ የጌትነት የመጀመሪያ ውድድር ደግሞ በ IAAF የዓለም ከ 20 ዓመት በታች ሻምፒዮና በፖላንድ በ ቢድጎዚዝ የተካሄደው ሲሆን በወቅቱ በውድድሩ ሁለት ጊዜ በውሃ መዝለሉ በመውደቁ ጌትነት የነሐስ ሜዳሊያውን በ 8 22.83 በ 3 ኛ ደረጃ ተሸላሚ ሆኗል። በኢንተርናሽናል ደረጃ ጌትነት የ3ሺ ሜትርን በተደጋጋሚ በመሮጥ ርቀቱት ማሸነፍ ችሏል። በተጨማሪም በ5ሺ በርቀቱ ልምድ ያለው አትሌት ነው።