በፋሲል ከነማ በኩል በግራ መስመር ተጨዋችነት የሚታወቀው ሳሙኤል ዮሐንስ ከሱፐር ስፓርት ጋር ከጨዋታው በኋላ ቆይታ አድርጓል። እንደሚታወቀው ሳሙኤል ዮሐንስ ዕድገቱ በባህርዳር የሕፃናት ማደጎ ውስጥ ሲሆን አሁን ደግሞ እሱ በተራው ለ40 ህፃናት እና ታዳጊዎችን ከእግርኳስ ከሚያገኘው ገቢ ላይ እነሱን ለማሳዳግ የበኩሉን እያደረገ ይገኛል ። ሳሙኤል ከጨዋታው በኋላ ከሱፑር ጋር ይህንና ሌሎች ጉዳዮች ላይ ቆይታ አድርጓል።
በቅደሚያ የውድድር ዘመኑን በእሱ እይታ በተመለከተ ?
“በጣም ደስ ይል ነበር። ዘንድሮ በተለይ ካለፉት ጊዜያት አንፀር ዘንድሮ የተሻለ ነበረ ብዬ የማስበው”
የአርባ ልጆች አባት ስለመሆኑ ?
“‘ያው ማለት ድርጅት ውስጥ እንደማደጌ መጠን እና ያሉት እፃናቶቹ ችግር ላይ ስለሆኑ ፣መልሼ እነሱን ማገዝ እንዳለብኝ ስለተሰማኝ ከእነሱ ጋር ጊዜዬን እያሳለፍኩ ባለኝ አቅም ሌሎች የሚረዷቸውን አካላት አየፈለኩኝ እነሱን እያሳደኩ ነው ያለሁት አሁን ላይ “
በባህርዳር የቤትኪንግ ቆይታ ወቅት የፋሲል ከነማ እና ሌሎችም ተጨዋቾች የህፃናት ማሳደጊውን ጎብኝተዋል፣ ድጋፍ አድርገዋል። በዚህ አጋጣሚ ሌሎች አካላት ድጋፍ እንዲያደርጉ የሚያስተላልፈው ጥሪ ?
” ባህርዳር ብቻ አይደለም በተለያዩ አካባቢዎች የተቸሩ ህፃናት አሉ እና ፣ በይበልጥ በስፓርት ውስጥ ያሉ አካላት በዚህ በጎ ስራ ላይ ቢሰማሩ መልካም ነገር ነው ብዬ እላለሁ። ምክንያቱም ተጨዋች በአንድ ጊዜ ውጤታማ የሆነ የለም። ብዙ ችግሮችን አልፎ ነው የመጣው እና ጥሩ ደረጃ ሲደርስ እታች ያሉትን ማየት አለብን ብዬ ስለማስብ ባህርዳር በነበረን ቆይታ ለዛ ነው ማሳያ የሆነውና ሁሉም ይህን ልምድ ቢለምድ ጥሩ ነው ብዬ አስባለሁ “
ካለፈበት ችግር አንፃር አሁን ላይ እደርሳለሁ ብሎ ስለማሰቡ ? የሚመክረውስ ምክር?
” ያው..ማናችንም ፍላጎት ካለን እና ከሰራን ውጤታማ የማንሆንበት ምንም ምክንያት የለም። ለዛ ማሳያ እኔ ሆንኩኝ እንጂ በጣም ብዙ ልጆች ይኖራሉ ብዬ አስባለሁ። በይበልጥ ደግሞ ያለፍክበትን ህይወት ተመኩሮ በእንደዚህ ሁኔታ ስትናገር ያንተን ፈለግ አይቶ በኳስ ለማደግ የሚፈልጉ አሉ እናትል ትምህርት ይሆናል ብዬ አስባለሁ “
የዘንድሮው ውድድር ሻምፒዮናነት መታሰቢያ ለማን ትሰጣለህ ?
” ባህርዳር ሕፃናት ማሳደጊያ ላሉት እህትና ወንድሞቼ እንዲሁም ለአቶ አሰግድ በረደር መታሰቢያ ቢሆን ደስ ይለኛል “