ትውልደ ኢትዮጵያውያን ዜናዎች

#ሊሊ -በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ ላይ በመሰለፍ በዕድሜ ትንሿ በመሆን አዲስ ታሪክ ይዛለች!

የሆላንዱ አያክስ አምስተርዳም የሴቶች ክለብ በአውሮፖ የሴቶች የቻምፒዮንስ ሊግ እየተሳተፈ ይገኛል። አያክስ በምድቡ በመጀመሪያው ጨዋታ በሮማ ተሸንፎ በሁለተኛ የፈረንሳዩን ፒኤስጂን አሸንፎ ሲጫወት በመጀመሪያው ጨዋታ የአሜሪካ ዜግነት ያላትና ትውልደ-ኤርትራዊት የ16 ዓመቷ ሊሊ ዮሐንስ የበርካቶችን ቀልብ ገዝታ ነበር ።
በአሜሪካ ስፕሪንግፊልድ ቨርጂኒያ ከተማ የተወለደችው የአማካይ ስፍራ ተጨዋቿ ሊሊ አያቷ በኢትዮዽያ እግርኳስ ታሪክ ብዙዎች የሚያስታውሱት እና በ6 ኛው የአፍሪካ ዋንጫ ወቅት ኢትዮጵያ ኮትዲቯርን በአዲስአበባ ስታዲየም 1ለ0 ስታሸንፍ ብቸኛውን ጎል ለኢትዮጵያ በ86ኛው ደቂቃ ያስቆጠሩት የአንጋፋው የበኩሬፅዮን ገ/ሕይወት የልጅ ልጅ ስትሆን አባቷ ኤርትራዊው ዳንኤል ዮሃንስ እና እናቷ ሰምሃር በኩረፅዮን ልጅ ናት ።
በአሁኑ ሰዓት የሊሊ ቤተሰቦች ከአሜሪካ ለቀው በሆላንድ መኖር አጀመሩ 7ኛ ዓመት አስቆጥረዋል።
እ.ኤ.አ. በ 2017 አባቷ አቶ ዳንኤል በIT ስራው ወደ ኔዘርላንድስ በ መምጣት ኑሮቿን መላው ቤተሰብ በአውሮፓ ካደረጉ በኃላ የኔዘርላንድ የመኖርያ ፍቃድ እና ዜግነት አላቸው ። እንደውም በቀጣይ ሊሊ ከአሜሪካ ብሔራዊ ቡድን ይልቅ ለኔዘርላንድ ብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ አንዷ ልትሆን ትችላለች የሚልም መረጃም ወጧት።
አሁን ላይ ግን ታዳጊዋ ሊሊ ለአያክስ አምስተርዳም የሴቶች ክለብ በሦስት አመት ውል ዘንድሮ ከፈረመች በኃላ ሰሞኑን እየተካሄደ ባለው በአውሮፓ ቻምፒየንስ ሊግ እና በአያክስ አምስተርዳም መለያ በ16 አመቷ በቻምፒየንስ ሊጉ ላይ በመሰለፍ በዕድሜ ትንሿ በመሆን አዲስ ታሪክ ይዛለች ።