ዜናዎች

ሉሲዎቹ የነገውን ከዮጋንዳ አቻቸው ጋር የሚያደርጉትን ጨዋታ አስመልክቶ መግለጫ ተሰጥቷል !

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ የምድብ ማጣሪያ ከዩጋንዳ አቻው ጋር ነገ ላለበት የመልስ ጨዋታ እና ከቀናት በፊት ስለ አደረጉት እንዲሁም የቡድኑን ወቅታዊ አቋም በተመለከተ ዋና አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው እና አምበሏ ሎዛ አበራ ወሎ ሰፈር በሚገኝው የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ጽ/ቤት ዛሬ መግለጫ ሰጥተዋል።
የሉሲዎቹ አሰልጣኝ ብርሃኑ ግዛው በመግለጫው እንደተናገሩት ከዮጋንዳ በነበረው ጨዋታ በድኑ 2 ለ 0 መሸነፉን አስታውሰው ፣ በተለይም አሰልጣኙ በመግለጫው ላይ እንደገለጹት ቡድኑ ጎል ሲቆጠርበት የመረበሽና የመደናገጥ ክፍተቶች ለሽንፈቱ ምክንያት እንደነበር ተናግረዋል።
በአንፃሩ የታዮ ክፍተቶችን ለማረምና በነገው ጨዋታ የተሻለ ለመሆን የጨዋታውን ቪዲዮ የቡድኑ አባላት በመመለከት ስህተቶችን በማስተካከል ቡድናቸው ለነገው ጨዋታ ዝግጁ መሆኑን ተናገረው ።
የቡድኑ አምበል ሎዛ አበራ በበኩሏ እሷን ጨምሮ የአጥቂው ክፍል ላይ የታየውን ክፍተት እንደ ቡድን አስተካክለው በነገው ጨዋታ በተሻለ ቅንጅት እንደሚቀርቡ ተናግራለች።የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ነገ በ10:00 ሰዓት ከዮጋንዳ አቻቸው ጋር በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ጨዋታቸውን የሚያደርጉ ይሆናል።
Photo ትዕንግርት የሴቶች ስፖርት