አፍሪካ ዜናዎች

ሉሲዎቹ ወደ ዮጋንዳ ጉዞ ጀምረዋል !

ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ  ከዩጋንዳ አቻው  የሚጫወቱት የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን አባላት  በዛሬው እለት ከቀኑ 5 ሰዓት ወደ ካንፓላ የሚያመሩ ሲሆን በአሁኑ ሰዓት በቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ይገኛሉ።
የፌዴሬሽኑ መረጃ እንደሚያመለክተው ሉሲዎቹ ባለፉት ቀናት በካፍ አካዳሚ ጠንካራ ልምምድ ሲሰሩ የነበሩ ሲሆን ሁሉም በመልካም ጤንነት ይገኛሉ። የሉሲዎቹ አባላት ወደ ቦሌ ጉዞ ከመጀራለው በፊት ለቡድኑ የምግብ አገልግሎት ሲያቀርብ የነበረው የጁፒተር ሆቴልም ኬክ በማቅረብ መልካም ምኞታቸውን ገልጸውላቸዋል።