ዜናዎች

ሉሲዎቹ ከደቡብ ሱዳን አቻቸው ጋር በነገው ምሽት የአቋም መለኪያ ጨዋታ ያደርጋሉ !

የኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ከደቡብ ሱዳን አቻው ጋር የመጀመሪያውን የአቋም መለኪያ ጨዋታ ነገ ሚያዚያ 2 ቀን 2013 ዓ.ም ከምሽቱ 12:30 በአዲስ አበባ ስታዲየም ያካሂዳል።ሉሲዎቹ ከመጋቢት 26 ቀን 2013 ጀምሮ በካፍ የልቀት ማዕከል ቆይታ በማድረግ ልምምዳቸውን እየሰሩ በጥሩ ዝግጅት ላይ ይገኛሉ። የነገውን ጨዋታ ማምሻው ላይ መደረጉ ምክንያት በአዲስ አበባ ስታዲየም እየተካሄደ በሚገኘው የአገር አቀፍ የአትሌቲክስ ውድድር ምክንያት መሆኑ  ፌዴሬሽኑ ገልጿል ።