ዜናዎች

ሉሲዎቹ በዮጋንዳ ተሸነፉ- የመልሱ ጨዋታ በአበበ ቢቂላ ስታዲየም ይደረጋል

የ2022 የአፍሪካ ሴቶች ዋንጫ ማጣሪያ የመጀመሪያ ዙር ከ የዮጋንዳቸው ጋር ዛሬ በሴንት ሜሪ ስታዲየም ያደረጉት ሉሲዎቹ በዮጋንዳ ብሔራዊ ቡድን ሽንፈትን አስተናግደዋል።
ጨዋታው በተጀመረ በሁለተኛው ደቂቃ ጎል ያስተናገዱት ሉሲዎች የጎል ሙከራዎችን ቢያደርጉም ጎል ማስቆጠር ሳይችሉ ቀርተዋል።
የኢትዮጵያ የሴቶች ቡድን በዮጋንዳቸው ሁለተኛ ጎል በ77ኛው ደቂቃ አስተናግደው 2ለ0 ተሸንፈዋል። የሁለቱ ቡድኖች ሁለተኛው ጨዋታ በአዲስ አበባ አበበ ቢቂላ ስታዲየም ማክሰኞ ጥቅምት 16 የሚደርግ ሲሆን በድምሩ ውጤት አሸናፊው ቡድን ወደ ቀጣዩ የማጣሪያ ዙር የሚያልፍ ይሆናል ።በቀጣይም ዙር ከኬንያ እና ከደቡብ ሱዳን አሸናፊውን የሚገጥም ይሆናል::