በሞሮኮ አስተናጋጅነት በ2022 ለሚከናወነው የአፍሪካ የሴቶች ዋንጫ ለማለፍ በመጀመሪያው የማጣሪያ ጨዋታ በዮጋንዳ 2 ለ 0 ተሸንፈው የነበሩት ሉሲዎቹ ዛሬ በ10:00 ሰዓት በአበበ ቢቂላ ስታዲየም በተደረገው የመልስ ጨዋታ ለማሸነፍ ያደረጉት ጥረት ሳይሳካ በመለያ ምቶች ተሸንፈው ከውድድሩ ውጪ ሆነዋል ።
የኢትዮጵያ የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ቀዳሚ ሆኖ በ21ኛው ደቂቃ በሴናፍ ዋቁማ ጎል ማስቆጠር ሲችሉ፣ ከእረፍት በፊት ካገኟቸው በርካታ የጎል ዕድሎች አምበሏ ሎዛ አበራ በ32ኛው ደቂቃ ጎል በማስቆጠር ከዕረፍት በፊት ሉሲዎቹ ጨዋታውን በድል አጠናቀው ነበር ።
በአንፃሩ ከሁለተኛው አጋማሽ በኃላ ሉሲዎቹ ከዕረፍት በፊት ያገኟቸውን በርካታ የጎል ማግባት ዕድሎች በሁለኛው አጋማሽ ማግኘት ሳይችሉ ቀርተዋል።
የተቃራኒው የዮጋንዳ ቡድን ጎል ለማስቆጠር የተሻሉ ሙከራዎች አድርገዋል። በአንፃሩ በሁለቱም ቡድኖች ጎል ሳይቆጠር ጨዋታው በመጠናቀቁ እና ፣መጀመርያ ዙር የማጣርያ ጨዋታ ዮጋንዳ 2 ለ 0 በማሸነፉ ጨዋታው አቻ ውጤት በመሆኑ ወደ መለያ ምት በማምራት ዮጋንዳ ማሸነፍ ችላለች። ዩጋንዳ ለአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የመጨረሻ ጨዋታቸውን ከደቡቡ ሱዳን እና ኬንያ አሸናፊ ጋር የሚያደርጉ ይሆናል።
በተያያዘ መረጃ የዮጋንዳ የሴቶች ቡድን ዛሬ በሉሲዎቹ ላይ በመጡት ውጤት የተደሰተች የዮጋንዳ ተጨዋቾች በደስታው ራሷን በመሳት ከጨዋታው በኋላ በመልበሻ ክፍል ውስጥ ህክምና ሲደረግላት ታይቷል። ኢትዮኪክ ከቡድኑ የህክም ባለሞያዎች ባገኘነው መረጃ መሠረት ተጨዋቿ በዛሬው የጨዋታ ውጤት በመደሰት ራሷን ከመሧቷ ውጪ የተጨዋቿን ጤንነት እና ተያያዥ ጥያቄዎች ላይ ተጨማሪ መረጃ ከመሥጠት ተቆጥበዋል። በአንፃሩ ተጨዋቿ በመልበሻ ክፍል የህክምና ዕርዳታ ከተደረገላት በኃላ ከመልበሻ ክፍል ወደ የተዘጋጀላቸው የቡድኑ ባስ እንደሌሎቹ ተጨዋቾች ራሷን ችላ መሄድ ባለመቻሏ ተሸክመው ሲወስዳትም ተስተውሏል።