ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

ለ45ኛ ጊዜ ሳንጃው ከ ቡንዬ የሚያደርጉት ስደተኛው ሸገር ደርቢ በቀዘቀዘ መልኩ ነገ ይካሄል !

ቀደም ባሉት አመታት ከፕሪሚየር ሊጉ ጨዋታዎች መካከል በጉጉት ይጠበቅ የነበረውና ከጨዋታው በፊት በሚኖሩ ሳምንታቶች ብሎም ቀናቶች ጀምሮ በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች ደምቆ በጨዋታው ቀን ደግሞ ምሽት ለሚደረግ ጨዋታ ከሌሊት ጀምሮ ቦታ ለማግኘት ወረፋ የሚያዝለት እና የአዲስ አበባ ስታዲየም በሁለቱ ክለብ ደጋፊዎች በተገኘው መድረክ ሲበዛ የሚደምቀው ሸገር ደርቢ ዘንድሮም በቀዘቀዘ መልኩ ከአዲስ አበባ ስታዲየም ውጪ የፊታችን ቅዳሜ ጥር 27/2015 ዓ.ም በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዪኒቨርስቲ ስታዲየም ከቀኑ በ9:00 ይካሄዳል።

በአዲስ አበባ ስታዲየም የተራዘመ ዕድሳትና የሊጉ ጨዋታዎች በሌሎች ስታዲየሞች መደረጉን ተከትሎ ሸገር ደርቢ በስደት ከሜዳው ውጪ በስደት  ለአራተኛ ጊዜ አዳማ ይካሄዳል ።

የ12ኛው ሳምንት ተስተካካይ የቤቲንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታ የሆነው ሸገር ደርቢ እና የሁለቱን ቡድኖች ከዚህ ቀደም እርስ በርስ  ያደረጓቸው ጨዋታዎች

 

ሳንጃው ከ ቡንዬ #

 

ሁለቱ ቡድኖች በቁጥር

👇

 

🔲 ሁለቱ ክለቦች በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ላይ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ 44 ጊዜ እርስ በርስ ተገናኝተዋል።

➡ቅዱስ ጊዮርጊስ 22 ጊዜ ሲያሸንፍ

➡ ቡና 8 ጊዜ አሸንፏል

➡ 14 ጨዋታዎች ደግሞ በአቻ ውጤት ተጠናቀዋል

.

🔲በእስከዛሬው የ44 ጊዜ የእርስ በርስ ግንኙነት 87 ኳሶች በሁለቱም ክለብ ተጨዋቾች በጋራ መረብ ላይ የተቆጠሩ ናቸው⚽

🔲 ቅዱስ ጊዮርጊስ 60 ጎሎችን በቡና መረብ ላይ በማሳረፍ የበላይነቱን ይዟል !

🔲 ቡና 27 ጎሎችን አስቆጥሯል

🔘ቅዱስ ጊዮርጊስ ከባለፉት 12 ጨዋታዎች 7ቱን አሸንፎ 4 አቻ ወጥቶ በአንዱ ብቻ ነው የተሸነፈው

🔘ኢትዮጵያ ቡና ከባለፉት 12 ጨዋታዎች መካከል 5ቱን አሸንፎ፤ በ5ቱ ጨዋታ ተሸንፎ በ2 ጨዋታ አቻ ተለያይቷል።

🔛ቅዱስ ጊዮርጊስ

በኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ላይ 25 ጊዜ ተሳትፏል..የዋንጫ ድል..15 ዋንጫ በማንሳት ከሁሉም ከፍ ብሎ በሻምፒዮኖች ማማ ላይ ተቀምጧል። ወቅታዊ የፕሪምየር ሊጉ ደረጃ. 2ኛ ደረጃ።

🔛 ኢትዮጵያ ቡና

የፕሪምየር ሊጉ ተሳትፎ..26 ጊዜ የፕሪምየር ሊጉ ድል 1 ዋንጫ( በ2003 ) ወቅታዊ የምሪምየር ሊጉ ደረጃ #9ኛ

በአጠቃላይ የቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ከ1991 ዓ.ም ጀምሮ የእርስ በረስ ግኑኝነት ታሪካዊ ዳራና የቁጥሮች መረጃ ከላይ በመጠኑ ለማቅረብ ተሞክራል ።

ይህ ለአመታት በሁለቱ ቡድኖች መካከል የቀጠለው ሰላማዊ ፉክክር እነሆ ጥር 27 ቀን 2015 ዓ.ም 45ኛውን የደርቢ ጨዋታ በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩንቨርስቲ ሜዳ ላይ ለማድረግ ቀን ተቆርጦ በመጠባበቅ ላይ ይገኛል።

# የጨዋታው ዳኞች

ኢንተርናሽናል አልቢትር ዶ/ር ሀይለየሱስ ባዘዘው ረዳቶች፦ ኢንተርናሽናል ረዳት አልቢትር ትግል ይግዛው እና ኢንተርናሽናል ረዳት አልቢትር ፋሲካ የኋላሽት 4ኛ ኢንተርናሽናል አልቢት ለማ ንጉሴ (ለሚ) በመሆን ይህንን ተጠባቂ የሸገር ደርቢ ጨዋታ ይመሩታል።

 

ቅዳሜ ጥር 27 ከቀኑ 9 ሰዓት የሚያደርጉትን የሸገር ደርቢ ጨዋታ ከቤትዎ ሆነው በዲኤስቲቪ ሱፐርስፖርት ልዩ 240 እና ልዩ2 239 ላይ በቀጥታ ይመ