የፋሲል ከነማው አጥቂ ሙጂብ ቃሲም የዘንድሮው ውድድር ዓመት ዐፄዎቹ ሻምፒዮና ይሆኑ ዘንድ የፊት መስመሩን ከፍተኛ ሚና ከተወጡ ተጨዋች ዋነኛው ነው።
ሙጂብ የዘንድሮው የውድድር ዓመት የመጀመሪያውን የሊጉን ጎል በአዲስ አበባ ስታዲየም አስቆጥሮ ፋሲል ከነማ ተጋጣሚውን ቅዱስ ጊዮርጊስን 1 ለ 0 አሸንፎ የድል በሩን የከፈተ ተጨዋችም ነበር።
በውድድር ዓመቱ ደግሞ ለክለቡ በ23 ጨዋታዎች ከተቆጠሩ 36 ጎሎች በሙጂብ ስም 20 ጎሎች ያስቆጠረ ሲሆን በ 2013 አ.ም በሊጉ ከኢትዮጵያ ብናው አብበከር ናስር በመቀጠል የሊጉ ሁለተኛ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪም ነው ። ከዚህ በተጨማሪም በክለቡ ደግም ሙጂብ በአጠቃላይ ክለብን ከተቀላቀለ ያስቆጠራቸውን የ ግብ ብዛት 50 ም አልፏል።የፋሲል ከነማው የጎል አዳኝ ሙጂብ ቃሲም ክለቡ የዋንጫ ባነሳበት ፕሮግራም ላይ ደግሞ ለግሉ የተበረከተለትን የክብር ሜዳሊያ ከእኔ ይልቅ የሚገባት ከጎኔ በችግራና በድካሜ ላልተለየች ብሎ ለባለቤቱ አጥልቋል።ከሻምፒዮኖቹ የጎል አዳኝን መጂብ ቃሲሚን ጋር ያደረግደው ቆይታ እንሆ:-;
ኢትዮኪክ :- የቅድሚያ እንኳን ደስ ያለህ
ሙጂብ ; አመሰግናለሁ
ኢትዮኪክ :- የውድድር ዓመቱ ለሙጂብ የስኬት ነበር ?
ሙጂብ :- በሚገባ ከዚህ በላይ ስኬት የለም። ያሳካነው ደግሞ የሀገሪቱን ትልቅ ዋንጫ ነውና ይህን ትልቅ ስኬት ነው።
ኢትዮኪክ :- የሁለተኛ ኮከብ ግብ አግቢነቱስ ?
ሙጂብ : – ዘንድሮ ለሶስተኛ ዓመት ነው ስፎካከር ። በዚህ መሀል ቡድኔ ዋንጫ እንዲያገኝ የሚቻለውን ሁሉ እያደረኩ ነበረ፣ በ ሶስት አመት ሶስት ዋንጫ አአግኝቻለሁ። ይህ ለእኔ ከኮከብም በላይ ትልቅ ክብር ነው። ለዋንጫ ስንፎካከር ዘንድሮ ለ ለሦስተኛ ጊዜ ነው ዋንጫውን አሸንፈናል። በኮከብ ግብ አግቢነቱም ጥሩ ነው።
ኢትዮኪክ :- በDstv ዘመን መጀመሪያ የሆነውን ዋንጫው ስታነሳው የተለየ ስሜት ነበረው ?
ሙጂብ : – DSTV ከመጣ ጀምሮ ኳሱ ስርሀት ይዞ አየተካሄደ ነው ማለት እችላለሁ ። እናም ይህን የዋንጫ ባለቤት በመሆናችን አጅግ በጣም ስሜቱ ታላቅ ነው
ኢትዮኪክ :- የወርቅ ሜዳሊያውን “ላንቺ ነው የሚገባሽ ብሎ” ለባለቤቱ አበርክቷል ስለሚባለዎውና የዋንጫ የደስታ ውሎ ?
ሙጂብ : – አዎ እውነት ነው። ከእኔ በላይ ለእሷ ስለሚገባት ነው። በብዙ መንገድ የእሷ ሚና ይበልጣል። እኔ ለዚህ እንድበቃ ከጎኔ ሆና ስታበረታታኝ ፣ ስትደግፈኝ የነበረችው ውዷ ባለቤቴ ናት ።ሽልማቱ እና ምስጋናው ለእሷ ነው የሚገባት ።
ኢትዮኪክ :- የዋንጫ ሽልማቱ ሲሰጥ ሙጂቤ በፋሲለ ደስ ስታዲየም ሙሉ ደጋፊ ባለበት ቢሆን ብሎ ተመኝቷል?
ሙጂብ : – አዎ! ገና ወደ ስታዲየሙ ስንገባ ምነለ ጎንደር ደጋፊው ሙሉ ድባብ ባለበት በሆነ ብዬ አስቤ ነበር ። እንደዛም ሆኖ ግን ጥቂት ደጋፊዎች ባለቡትም በሐዋሳም ዋንጫውን ያነሳነበት ድባብ ፣ ደስታው ልዬ ነው።