ሚካኤል ጆርጅ የሀዲያ ሆሳዕና የአማካይ ስፍራው ተጨማሪ ሃይል በመሆን ጠንካራ ሚና በሃዋሳ ቆይታው ተጫውቷል። በውድድሩ የመጨረሻው ቀን ሚካኤል ከሱፐርስፓርት ጋር የሚከተለውን ቆይታ አድርጓል።
አራተኛ ደረጃ ይዘው ማጠናቀቃቸውን በተመለከተ ?
“ቡድኑ እንደመጣበት መንገድ ሁለተኛ ደረጃ ለእኛም ይገባ ነበረ ። እዚህ ሃዋሳ ላይ ስንመጣ ታዳጋዎቹ ከተወሰኑ ልምድ ካላቸው ጋር ነው አጣምሮ ለመጫወት የሞከርነው። የመጀመሪያውን ጨዋታዎች በ8 ተጨዋቾች ነበር የጀመርነው። እሱ ውጤት ተፅእኖ አድርጎብናል እንጂ እዚህ ቦታ ላይ መገኘት አልነበረብንም ። ከቡና የጣልነው ውጤት ፣ ከሰበታ የጣልነው ውጤቶች እነጂ ሁለተኛ ደረጃ ለእኛም ይገባ ነበረ። ነገር ግን እግዚአብሔር የፈቀደው አራተኛ ደረጃ ነው ተመስገን ነው”
የውድድር ዘመኑ የዋንጫ ተፎካካሪ ከመሆናቸው እንፀር ያስቆጭ ነበር ?
” እጅግ በጣም። አሁን ለሁለተኛ ፤ ለሶስተኛ ቡድን የተሰራ ሳይሆን ለዋንጫ የተሰራ ቡድን ነበር።ሙሉ ለሙለ የዋንጫ ቡድን ነበረ፤ ከአዲስ አበባ ከወጣን በኃላ ነው ነገሮች ሙሉ ለሙሉ መበላሸት የጀመሩት።በአንዳንድ ጉዳዮች በተያያዘ። ከዛ በኃላ ባህርዳር ላይ ለማስተካከል ተሞከረ። ነገሮች ሊፈቱ አልቻሉም። እዚህ ስንመጣ ደግሞ የእግርኳስ ከባዱ ሁኔታ ተፈጠረ።ነገር ግን ክለቡ ለማገገም ወጣት ተጫዋቾችን አምጥቶ ነበረ፤ ይህን ደረጃ ይዘን ጨርሰናል እንጂ ለዋንጫ የተሰራ ቡድን ፤ ዋንጫ የሚበላ ቡድን ነበረ የሀዲያ ሆሳዕና ቡድን።
ከተወሰኑ ጨዋታዎች በኋላ ከተከላካይነት ወደ ተከላካይ አማካይነት በመጫወት ጎል ማስቆጠረም ችሏል?
” አዎ …ከዚህ በፊትም በአዳማ ከተማ ከአሰልጣኝ አሸናፊ በቀለ ጋር በሲዳማ ቡና ቡድኑ በሚቸገርበት ሰአት በተለይ ክልሎች ላይ ስንወጣ ተጨዋቾች በሚጎዱ ሰአት ያጫውተኝ ነበረ። እና በፊትም የማውቀው ቦታ ነው። አሁንም መጥቼ ስጫወትበት ደስተኛ ሆኜ ነው። ለታዳጊዎቺ አመራር መስጠት እና የተወሰነ ተሳትፎ ማድረግ ነው። ደስ የሚል ቦታ ነው ተመችቶኛል በጣም”