ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ለዋንጫው ነው እየተጫወትን ያለነው”ሙጂብ ቃሲም

ለፋሲል ከነማ በዛሬው ጨዋታ ሁለት ጎሎችን ያስቆጠረው እና በግሉ ያስቆጠረውን የሊጉን የጎል መጠን ወደ 15 ያደረሰው ሙጂብ ቃሲም ከዛሬው ጨዋታ በኃላ የሚከተለውን ብሎ ነበር ።በቅድሚያ የተሰማውን ደስታ በመግለፅ ይጀመራል ” ያው ደስ ይላል ። በተከታታይ እኔም ሁለት ጎሎች አስቆጥሪያለውና በዚህ ሁለት ጨዋታ ስድስት ነጥብ አግኝተናልም። እናም በጣም ደስ ብሎኛል” ካለ በኃላባለፈው አመት በኮሮና ምክንያት ሲቋረጥ ሊጉን በ14 ጎል እየመራ ነበረ : ዛሬ ይህንን ማለፉን አስመልክቶ የተሰማውን ሙጂብ ቃሲም ሲቀጥል ” አምና በኮሮና ምክንያት ተቋርጦ 14 ጎሎች አግብቼ ነበር ። ዘንድሮም ይህን አልፊያለው። በየዓመቱ መሻሻሌ የተሻለ ጎል ለማስቆጠር ነው። ለዚህም ጥረት እያደረኩ ያለሁት። እናም በጣም ደስ ብሎኛል” ብላል ሙጂብ ከቡድኑ ጋር ሻምፒዮናነት ይታየዋል ለሚለው ጥያቄም ሲመልስ ” አዎ ! በሚገባ። የእኛ የመሪነት ልዪነት 11 ደርሷል ስለዚህ ለዋንጫ ነው እየተጫወትን ያለነው።ሁሉንም ጨዋታ በትኩረት ነው አየተጫወትን ያለነው ለዛም ነው ። ኢንሽ አላህ ጥሩ ነው ” በማለት ገልጿል።በባህርዳር ቆይታቸው ልዩ ትዝታ እንዳለው ለተጠየቀው ” በጣም…ባህርዳር ላይ ብቻም ሳይሆን ጅማም ላይ ያው ትዝታው አለ ። ይህም ያለ መሸነፋችን ነው።ይሄ ሜዳ ደግሞ ከዚህም በፊት የምናውቀው ስለሆነ እንደ ጎንደር ወይም በሜዳችን እንደምንጫወት አድርጌ ነው የማስበውና ጥሩ ትዝታ አለኝ” በማለት ሙጂብ ተናግሯል።