ዜናዎች

” ለአፍሪካ ዋንጫ ብናልፍ ለብዙ ተጨዋቾች የውጪ ፕሮፌሽናል ዕድል ይፈጠራል ” ➖አስቻለው ታመነ

የዋልያዎቹ ተከላካይ አስቻለው ታመነ የዛሬውን ጨዋታ አስመልክቶ ከኢትዮ ኪክ ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።በቅድሚያ ወደ አፍሪካ ዋንጫው ለማለፍ ሁለት ወሳኝ ተከታታይ ጨዋታዎችን በአስቻለው በኩል የዝግጅት መንፈስ ምን ይመስላል ለሚለው አስቻለው ሲመልስ ” ለዚህ ወሳኝ ጨዋታ በእኔ ብቻ ሳይሆን በሙሉ የቡድን ጓደኞቼ ተዘጋጅተን በከፍተኛ የማለፍ ተስፋ ይዘን እየሰራን ነው “
የዋልያዎቹ የአሁኑ ስብስብ ጠንካራ ጎኑ በአንተ እይታ የትኛው ነው ለሚለው ‘ ቡድናችን በሁሉም መልኩ ጠንካራ ጎን አለን።  ከማላዊ ጋር ያደረግነው የወዳጅነት ጨዋታ እንደ ቡድን ለመጫወታቸውን መገለጫው ነው ። በተለይ የአሰልጣኙ ፍልስፍና ላለነው ልጆን አመቺ ስለሆነ ይህ ደግሞ ተጠቅሞናል ብዬ አስባለሁ ። በሁሉም በኩል በማጥቃቱም ፣ በመከላከሉም ቡድኑ ጥሩ ነው። በአጭሩ ሙሉ ቡድኑ ማለት እችላለሁ። ስለዚህ ስብስቡ ከዛ አንፃር በሁሉም መልኩ ጠንካራ ነው ማለቴ ነው ” በማለት የዋልያዎቹ ተከላካይ ምላሹን ሰጥቷል።
ለአፍሪካ ዋንጫ  ብሂራዊ ቡድኑ ቢያልፍ አስቼ ምን ያደርጋል  ለሚለው ጥያቄ አስቻለው ሲመልሱ” ለአፍሪካ ዋንጫ ብናልፍ በእግር ኳስ ህይወቴ ካሳካዋቸው ነገሮች በመጀመሪያ እና በግንባር ቀደምትነት የሚቀድም ታሪክ ይሆንልኛል። ወደ አፍሪካ ዋንጫ ካሳለፈ ቡድን ጋር በመኖሬ ማለት ነው። ከዛ በመቀጠል  ለብዙ ተጨዋቾች የውጪ ፕሮፌሽናል ዕድል ይፈጠራል ። ወደ ውጪ ወጥቶ በፕሮፌሽናልነት የመጫወት ዕድል ይፈጠራልና በጣም አሪፍ ነገር ነው ። ስለዚህ ከእግዚአብሔር ጋር አልፈን ብናወራበትም ይሻላል ብዬ አስባለሁ ” በማለት ተናግሯል