አትሌቲክስ ዜናዎች

” ለንደን የመጣሁት ለማሸነፍ ነው “አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

አትሌት ቀነኒሳ በቀለ እሁድ ከሚደረገው የለንደን ማራቶን አስቀድሞ በሰጠው አስተያየት አሁንም የረጅም ርቀት ታላቁ አትሌት መሆኑን ገልጿል።

የ 40ዓመቱ ታሪክ አይሽሬው አትሌት ቀነኒሳ በቀለ ሶስት የኦሎምፒክ ወርቅ ሜዳሊያ ፣ 17 የሀገር አቋራጭ ክብሮች እንዲሁም የ 5,000 እና 10,000ሜትር ሪከርድን ለአስራ አምሰት እና አስራ ስድስት ዓመታት የግሉ አድርጎ አቆይቷል።

 

” ራሴን ከኪፕ ቾጌ ጋር ማፎካከር አልፈልግም ” የሚለው ቀነኒሳ ” ከላይ የተጠቀሱት ክብሮች እና የውድድር መድረኮች አንፃር እኔ ምርጡ ነኝ ” ሲል ተደምጧል።

አያይዞም ” አሁን ላይ በአካል ብቃቱ ጥሩ ነኝ ፣ ጥሩ ውጤት እንደማመጣ እጠብቃለሁ ለንደን የመጣሁት ምኞቴም ሆነ እቅዴ ለማሸነፍ ነው ” ሲል ከፊቱ ስለሚጠብቀው ውድድር ሀሳቡን አካፍሏል።

በማራቶን ታሪክ ሁለተኛው ፈጣን ሰዓት ያለው ቀነኒሳ በቀለ በለንደን ማራቶን ከኬንያው አሞስ ኪፕሩቶ ብርቱ ፉክክር ይጠብቀዋል።

በለንደን ማራቶን የአምናውን የርቀቱ አሸናፊ ሲሳይ ለማ ጨምሮ ብርሀኑ ለገሰ እና ሞስነት ገረመው ሀገራችንን ወክለው የሚወዳደሩ ይሆናል።

የሁለት ጊዜ የበርሊን ማራቶን አሸናፊው ቀነኒሳ ” 2:01.41 ሰዓት በቂ አይደለም ከዚህ የተሻለ ሰዓት ማስመዝገብ እፈልጋለሁ ” ሲል አስተያየቱን ሰጥቷል።

በሽር አብዲ እና ቪንሰንት ኪፕቹምባ ሌሎች በውድድሩ የሚሳተፉ ስመጥር አትሌቶች ናቸው።

@ቲክቫ ስፖርት

One thought on “” ለንደን የመጣሁት ለማሸነፍ ነው “አትሌት ቀነኒሳ በቀለ

Comments are closed.