የሲዳማ ቡና ስፓርት በቅርቡ ካስፈረማቸው የውጭ ተጨዋቾች መካከል አንዱ የቤኒን ብሔራዊ ተጨዋቾች የሆነው ግብ ጠባቂ ፋቢየን ፋርኖል ይጠቀሳል። በቀድሞ በፈረንሣይ ቦርዶ የተወለደው እና በቅርቡም የቤኒን ብሔራዊ ቡድን ለአፍሪካ ዋንጫ ማጣሪያ ፋቢያን የመሠለፍ ዕድልም አግኝቷል። ቤኒናዊው የ36አመቱ ግብ ጠባቂ ፋቢያን በዛሬው ምሽት ጨዋታ ለሁለተኛ ጊዜ ተሰልፎም ተጫውቷል ።ቡድኑም ማሸነፍ ችሏል ። አዲሱ የሲዳማ ቡና ግብ ጠባቂ ፋቢየን ፋርኖል በእግር ኳስ ህይወቱ በአውሮፓ ከ10 በላይ ክለቦች የተጫወተ ሲሆን አሰልጣኝ ገብረመድህን ኃይሌ የሚሰለጥኑን የፋቢየን ሲዳማ ቡናዎች ከወራጅ ቀጠናው ለማምለጥ ከፍተኛውን ጥረት ይዘዋል። ከቀናት በፊት ቡድኑ አዳማን ከተማን ሶስት ለባዶ ሲያሸንፍ በዛሬው ምሸት ጨዋታ በደግሞ ወልቂጤን 1 ለ0 አሸንፈው ሶስት ነጥብ ይዘው ወጥተዋል።
የሲዳማ ቡናው አዲሱ ግብ ጠባቂም በሁለቱም ጨዋታ ድንቅ ብቃቱን አሳይቷል ።በዋናው የፈረንሳይ ሊግ በቦርዶ ክለብን እ.ኤ.አ. ከ 2002 ዓ.ም በ17 ዓመቱ የመጫወት ዕድል የጀመረው የ36 አመቱ ግብ ጠባቂ የሲዳማ ቡና አዲሱ ቤኒናዊውን ተጨዋች ለኢትዮኪክ ሰለ አዲሱ ቡድኑ የሚከተለውን ብሏል
” ወደ ኢትዮጵያ በመምጣቴ ትልቅ ነገር ነው። ከምንም በላይ ደግሞ ለሲዳማ ቡና የተሰለፍኩበት ጨዋታ ላይ ማሸነፋችን ትልቅ ነገር ነው ። በርግጥ እንደ ፕሮፌሽናል ተጫዋች ሁልጊዜ አዲስ ፈታኝ የሚመስሉ ነገሮችን መሞከር እወዳለሁ። እኔ በግሌ ዕድለኛ ነኝ አዲስ ባህል አዲስ አገር መጥቼ መጫወት በመቻሌ ወደ ኢትዮዽያም መምጣቴ በዋነኝነት አዲስ የሆነ ባህል፣ አዲስ የእግርኳስ ልምድና አንድ የአፍሪካ እግር ኳስ አንድ አካል የሆነውን ጥሩ አጋጣሚ ለመጠቀም ነው ። እናም በወደ እዚህ መጥቼ ለሲዳማ ቡና በመጫወቴ ደስተኛ ነኝ ። በተጨማሪም ቀጣይ ጨዋታዎች ከቡድኑ ጋር በድል ለማሸነፍ እነጥራለን” ሲልም ቤኒናዊው ፋቢየን ፋርኖል ተናግሯል።