በግብፅ ፕሪሚየር ሊግ ለተከታታይ አመታት ድንቅ ብቃቱን በማሳየት ላይ የሚገኘውና ዘንድሮ የግብፅ ሊግ የተሳካ ጊዜን በማሳለፍ የሚገኘው ሽመልስ በቀለ ለኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወሳኝ ጨዋታ ዛሬ አገሩ ደርሷል።በግብፅ ሊግ ከከፍተኛ ጎል አስቆጣሪዎች አንዱ የሆነው የአማካይ ስፍራው ሽመልስ በቀለ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ቀጣይ ሁለት ጨዋታዎችን ለአፍሪካ ዋንጫ የማለፍ እድሉን አስመልክቶ ሃሳቡን ኢትዮኪክ አካፍሎናል ” የአፍሪካ ዋንጫን ለማለፍ ዘንድሮ ታልቅ ፍላጎትና ዕዱሉ አለን። በግሌ ለዚህ ጨዋታ ከፍተኛ የማሸነፍ ስሜትና ትልቅ ጉግት ይዥ ነው ቡድኔን የምቀላቀለው” ካለን በኃላ ከማዳጋስካር ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ ወሳኝ ስለመሆኑ ሽመልስ ሲቀጥል ” ከምንም በላይ የመጀመሪያው ጨዋታ ስናሸንፍ ነውና ሁለተኛውን የምናስበው ።በመጀመሪያ ከማዳጋስካር ጋር የምናደርገው ጨዋታ ከምንም በላይ በትልቅ ግምት የምጠብቀው ነው። በርግጥ ሁለቱን ጨዋታዎች ወሳኝ ቢሆኑም ይሄኛው ለእኛ ትልቅ ታሪክም ሆኖ ነው የሚሰማኝ። ይህንን ጨዋታ ከበፊቱ የበለጠ ትኩረት ሰጥቼ መጫወት ነው የምፈልገው። ከጓደኞቼ ጋር እግዚአብሔር ይረዳናል ብዬም አስባለሁ ” በማለት ምላሹን ሽመልስ ሰጥቶናል በዘንድሮ የግብፅ ሊግ በሶስት ተከታይ ጨዋታዎች የማሸነፊያ ጎሎች በማስቆጠር ክለቡ ምስር ኤል ማካሳ ሶስት ነጥብ ይዞ እንዲወጣ ያስቻለው ሽመልስ በቀለ በክለቡ ወሳኝ የጎል ማስቆጠሩ ሂደት በብሔራዊ ቡድኑም ይቀጥላል ለሚለው ጥያቄ ሽመልስ ሲመልስ “ከክለብ በላይ ሀገር ይቀድማል። ስለዚህ ለሃገሬ ማድረግ ያለብኝን ሁሉ በማድረግ የማዳካስካሩን ጨዋታ ለማሸነፍ ነው የምፈልገው ። ይህንንም በጥሩ ብቃት እና ውጤት ለመወጣት ከአሰልጣኞቼ እና ከጓደኞቼ ጋር እግዚአብሔር ያግዘናል እላለሁ። የማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድንም ለኢትዮጵያ ከፍተኛ ግምት በመስጠት በትዊተር ላይ ሲፅፉ ይታያል። እኛም ቲም ውስጥ ጓደኛዬ ፖውሎ የማዳጋስካር ብሔራዊ ቡድን ተጨዋች ነው። ጥሩ ተጨዋች ነው። ግን እንዳልኩት ክለብ እና ሀገር የተለያየ ነው። በእኔ በኩል የማዳጋስካር ጨዋታ በትልቅ የማሸነፍ ስሜት ነው የምጠብቀው ” በሚል ኢትዮጵያዊው ድንቅ የአማካይ ተጨዋች ሽመልስ በቀለ ለኢትዮኪክ ምላሹን ሰጥቶናል።