ከአራት ዓመት በፊት በቶኪዮ ኦሎምፒክ ላይ በወርልድ ቴኳንዶ ስፖርት በመሳተፍ ለኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ ዲፕሎማ በማግኘት አድናቆት ያተረፈው ሰለሞን ቱፋ ዛሬ በማህበራዊ ገፁ ላይ ይህን አስፍሯል።
የሚገባኝን ክብርና ሽልማት አለማግኘቴን ፣ ለሀገሬ መድማት መሰበሬን እንደክብርና ክፍያ ቆጥሬ አለፍኩት ፣ እንደልማዴ ለሀገሬ ባለኝ ልምድ እና ችሎታ ተወዳድሬ መክፈል ያለብኝን ዋጋ እንዳልከፍል መደረጌን ግን ፣ መቋቋም አልቻልኩም ።
ምናልባተ አልቅሼ የተጎዳውን ስሜቴን መግለፅ አልችል ይሆናል። በመላው አለም የምትገኙ ኢትዮዸእያን እና የስፓርት ቤተሰቦች ይሄንን የደረሰብኝን በደል እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ ።
በኢትዮዽፒያ ስፓርት አመራር ላይ ባሉ ግለሰቦች በተደጋጋሚ በደል እንዳደረሱብኝ ይታወቃል ። ያ ሁሉ አልፎ ዛሬ ላይም ነጭ ላቤን አፍስሼ ሁሉ ነገሬን ሳልሰስት ለረጅም ግዜ ስዘጋጅ በነበርኩበት የ 2024 የፓሪስ ኦሎምፒክ በሴኔጋል ላይ በሚዘጋጀው የአፍሪካ ማጣሪያ ውድድር ላይ ለመሄድ እየተዘጋጀው ባለሁበት ሰአት ለዚው ዝግጅት ከነበርኩበት ሀገረ አሜሪካ ውድድሩ ሲቃረብ ስልጠና አቆርጬ እንድመጣ በፌዴሬሽኑ በኩል ደብዳቤ ደርሶኝ በሱ መሰረት ከመጣው ቡሀላ ለጉዞ ጥቂት ቀናቶች ሲቀሩት መቅረቴን ተመዝግቤ የነበረውን ምዝገባ በኢትዮዽያ ወርልድ ቴኳንዶ ፌዴሬሽን በኩል እንደተሰረዘ ከአለም አቀፉ ውድድር አዘጋጅ መረጃ ደርሶኛል ስለ ሁኔታው ግን በፌዴሬሽኑ በኩል በተደጋጋሚ ብደውል መልእክት ብልክም ስልክም አያነሱልኝም ለምን እንደዚ እንዳደረጉ እና እኔን እና ሀገርን በተደጋጋሚ መጉዳት እንደተፈለገ በግልፅ ሊነግሩኝ አልቻሉም ። የተወደዳቸሁ ዉድ ቤተሰቦቼ እና መላው የኢትዮጵያ ሀዝብ ስትደግፉኝ ስታበረታቱኝ የነበራቹ ሁሉ የደረሰብኝን በደል እወቁልኝ።
,ሰለምን ቱፋ