ፋሲል ከነማ ስፖርት ክለብ ቡድኑን ለማጠናከር ከፍተኛ ስራዎችን እየሰራ የሚገኝ ሲሆን ለአመታት በህመም ምክኒያት ከሜዳ ርቆ የነበረውን ሀብታሙ ተከስተን ከቡድኑ ጋር በመቀላቀል በቂ የዝግጅት ጊዜ በመስጠት በልምምድ ብቁ ሆኖ በመገኘቱ ውሉን በማደስ አስፈርሟል።ፋሲል ከነማ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሻምፒዮን ሲሆን ከፍተኛ ሚና የነበረው ሀብታሙ ተከስተ (ጎላ) በአፄዎቹ እንዲሁም በኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን መለያ በአማካይ ተከላካይ ቦታ ላይ አስደናቂ እንቅሰቃሴ ሲያሳይ እንደነበር የሚታወስ መሆኑን የክለቡ መረጃ ያመለክታል::