ዜናዎች

⭕ እድሜ ጠገቡ የአዲስ አበባ ስታዲየም ሊፍት እየተገጠመለት ይገኛል

 

– የVIP ሰዎች ከዘህ በኃላ ትሪቡን የሚገቡት በደረጃ ሳይሆን በሊፍት ቀጥታ ይሆናል !

👇
በቀድሞ መጠሪያዉ ቀኃሥ ስታድየም በአሁኑ ስያሜዉ የአዲስ አበባ ስታዲየም ላለፉት አራት ዓመታት ዕድሳት ላይ የነበረ መሆኑ ይታወቃል ፣ እናም “መቆየት ደጉ” እንደሚባለው አሁን ላይ እድሜ ጠገቡ ስታዲየም በትሪቡን በኩል ሊፍት እየተገጠመለት መሆኑን ኢትዮኪክ ማረጋገጥ ችላለች።

ኢትዮኪክ ጉዳዩን አስመልክቶ ባገኘነው መረጃ የአዲስ አበባ ስታዲየም ዕድሳቱ በአብዛኛው የተጠናቀቀ ሲሆን
በጥላ ፎቅ እና ትሪቡን በኩል የወንበር ገጠማው አሁንም ያልተጠናቀቀ እንደሆነና ለጥላ ፎቅ የሚገጠሙት ወንበሮች እዛው ስታዲየም ቢገኙም ወንበሮቹ እስካሁንም ሳይገጠሙ በስታዲየሙ ተቀምጠው ይገኛል ። ይሁንና የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ሰኔ ከሚደረጉ ሦስት ጨዋታዎች በፊት ይደርሳል ተብሎ ይጠበቃል።

ሌላው በዘመናዊ መልኩ ተሰርቶ ያለቀው እና በአንድ ጊዜ አራት ቡድኖችን ማስተናገድ የሚችል የመልበሻ ቤቱ ሲሆን
የተጨዋቾች የውሃ ችግር ተቀርፎ ከጨዋታው በኋላ እዛው ሻወር እንዲወስዱ እና የውሃ ችግሩን ለማቃለል ትልቅ የውሃ ታንከርም ተገጥሟል።

ከአዲስ አበባ ስታዲየም ዕድሳት ጋር ሌላ ትኩረትን የሳበው
ለVIP እና ባለስልጣናት እየተሰራ ያለው ሊፍት ሲሆን፣ ከዚህ በኃላ የክብር እንግዶች እና የVIP ሰዎች በትሪቡን በኩል ቀጥታ የVIP room በኩል አድረገው ቀጥታ ወደ መቀመቻቸው እንጂ የትሪቡንን ደረጃ ወጥተው በተመልካች በኩል አይገቡም ማለት ነው።

ከላይ በጥላ ፎቆች ጀርባ ያሉት ክፍሎች ሰፋ ብሎ ለጋዜጠኞች ምቹ ሆኖ ተሰርቷል። የድሮ በመስታወት ውስጥ ጋዜጠኞች ቀረፃ የሚያስተላፉበት ክፍል አሁን ለVIP እና ለእንግዶች ሻይ ቡና የሚሉበት ክፍል ይሆናል ማለት ነው።

ሌላው የአዲስ አበባ ስታዲየም የምሽት ጨዋታ የስታድየሙ ፖውዛ በመጥፋት በተደጋጋሚ ተቋርጦ ያውቃል። እናም በቀጣይ ከብርሃን ጋር የሚገጥመው ችግር ለማቃለል በአራቱም አቅጣጫ የነበሩ የድሮዎቹ ፖውዛዎች ተነቅለው ሌላ አዲስ ፖውዛ ተደርገዋል።
አዲሶቹ ፖውዛዎች ክብ ሆነው ጠራትና የብርሃን ሃይላቸው ከዚህ ቀደም ከነበሩት የተሻሉ እንደሆኑ ታውቋል። እንደመረጃው ከሆነ በአንዱ ምሰሶ ላይ አስራ አምስት ፣ አስራ አምስት ፖውዛዎች ተገጥሟል። ይህም በአራቱም አቅጣጫዎች 60 ፖውዛዎች ተገጥመዋል ማለት ነው።
በትሪቡኑ ጣሪያው ላይ ስድስት የተገጠሙ ሲሆን በተጨማሪም በትሪቡን ፊትም ስድስት አጠቃላይ 12 ተገጥመዋል። የተገጠሙት የስታደየሙ መብራቶች በአጠቃላይ 72 ፖውዛዎች ሲሆን እነዚህ ፖውዛዎች 96 አምፖሎች አላቸው ተብሏል።

እንደሚታወቀው የዲኤስ ቲቪ የምሽት ጨዋታ ለማስተላለፍ አንዱ መመዘኛው የብርሀን መጠን ሲሆን አሁን ላይ የአዲስ አበባ ስታዲየም በአዲስ በተገጠሙት ፖውዛዎች ይህንኑ የሚያሟላ ብርሃን ተገጥሞለታል።

የትሪቡኑ ግቢም ከወራት በፊት በፊት ለፊት ላይ የነበሩ መኪና እና ሞተር አከራዮች ከተነሱ በኃላ አሁን ላይ ፌዴሬሽኑ ሰፊ ግቢ በማድረግ አጥረውታል። ሰፊ ጊቢው ፣ቀጣይ መኪናዎች ቀጥታ ዋና ግቢ በማድረግ ብዙ መኪና ፣አንድ ጊዜ መያዝ እንዲችል እንደሚደረግ ነው መረጃው ለኢትዮኪክ የዘገበው።