ቡድን ዝግጅቱን በተፈጥሮ ሜዳ አድርጎ የሚጫወተው አርቴፊሻል ሜዳ መሆኑ የቡድኑ ውጤት ተፅኖ አያመጣም ብለዋል!
👇
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በአፍሪካ ሀገራት ዋንጫ (ቻን) የመጨረሻ ዙር ማጣርያ ከሱዳን ጋር ለሚያደርገው ጨዋታ የመጨረሻ የአዲስ አበባ ዝግጅቱ ነገ ማለዳ በአዲስ አበባ ስታዲየም ካደረገ በኃላ ሌሊት ላይ ወደ ሊቢያ የሚያቀና ይናሆል::የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን አስመልክቶ ዛሬ በፌዴሬሽኑ መሰብሰቢያ አዳራሽ ጋዜጣዊ መግለጫ ተሰጥቷል።
በመግለጫው ላይ እንደጠቆመው ቡድኑ የሀገር ቤት ዝግጅቱን ነገ ረፋድ በማጠቀቅ በነገው ዕለት ምሽት ላይ ጨዋታዎቹን ወደ ሚያደርግበት ሊቢያ ቤንጋዚ ያመራል ተብሏል:: በተጨማሪም ዋልያዎቹ በሊቢያ ቤንጋዚ በሚያደርጉት የመጀመሪያው ጨዋታ ባለሜዳ መሆናቸውን ተከትሎ ጨዋታው በዝግ ለማድረግ መታቀዱን ተገልጿል::
የፌዴሬሽኑ ፀሀፊ አቶ ባህሩ ጥላሁን ይህንኑ ሲያብራሩ ዋልያዎቹ ሊቢያ ቤንጋዚ ላይ የሚካዱት ጨዋታ በርካታ ሱዳናውያን በሊቢያ ኑራቸውን ማድረጋቸውን ተከትሎ የካፍ ውድድሮች ላይ ሱዳናዊያን ተመልካቾች ሜዳው ሞልተው የሚታዩበት መሆኑን በመጥቀስ ኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የሜዳ አድቫንቴጁን በመጠቀም ጨዋታውን በዝግ ለማድረግ ጥያቄ ለካፍ ማቅረባቸውን ተናግረዋል። ይሁንና በዝግ ቢሆንም የተጋጣሚ ቡድን አባላትን ነፃ ትኬቶች የሚገቡበት ት ዕድል ይኖራል ብለዊል።የዋልያዎቹ በአዲስ አበባ ስታዲየም የአምስት ቀናት ልምምዱን ተከትሎ በጋዜጣዊ መግለጫ ላይ ዋና አሰልጣኝ መሳይ ተፈሪ በሚገባ ተዘጋጅተናል ብሏል::
በአንፃሩ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ዝግጅቱን በተፈጥሮ ሜዳ ላይ አድርጎ የሚጫወቱት አርቴፊሻል ሜዳ ላይ መሆኑ የቡድኑ ውጤት ተፅኖ አያመጣም ለሚለው ጥያቄአሰልጣኝ መሳይ ችግር የለውም ተፅኖም አይፈጥርም በማለት ምላሽ ሰጥቷል::
የኢትዩጵያ ብሄራዊ ቡድን ቤንጋዚ ላይ ጨዋታዎቹን ታህሳስ 13 እና ታህሳስ 16 የሚያደርግ ይሆናል::