ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

⭕የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች የ23ኛ ሳምንት ከነገ ጀምሮ በሃዋሳ መካሄድ ይቀጥላሉ

🕳ከ28ኛ እስከ 30ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ?
👇


የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ጨዋታዎች ከ23ኛ ሳምንት ጀምሮ በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም እንደሚካሄድ የፕሪሚየር ሊጉ አክሲዮን ማህበር  ቀደም ብሎ  ማሳወቁ ይታወሳል።

የሊጉ መርሐ ግብር በኢትዮጵያ ዋንጫ ምክንያት ከተቋረጠ በኋላ ወደ ውድድር ሲመለስ የ23ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሃዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም  ከነገ ከሚያዚያ 24 እስከ 27 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚካሄዱ የሊጉ አክሲዮን ማህበር  አመልክቷል።

ከ28ኛ እስከ 30ኛ ሳምንት የሊጉ ጨዋታዎች በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚከናወን ማህበሩ ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወቃል።
የሊጉ ውድድር ሰኔ 23 ቀን 2016 ዓ.ም እንደሚጠናቀቅ ተጠቁሟል።