ዜናዎች

የፌዴሬሽኑ ፕሬዝዳንት በተገኙበት የጨዋታው ምርጥ የ5 ሊትር ዘይት እና 25 ኪሎ ሩዝ ተሸልሟል!

👇
የድሬዳዋ ከፍተኛ ዲቪዚዮን እግር ኳስ ዓመታዊ ሻምፒዮና በ14 ክለቦች መካከል ዛሬ በድምቀት ተጀምሯል።
በመክፈቻው ስነ ስርዓት የኢትዮጲያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳያስ ጅራ የድሬዳዋ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዝዳንት ኮምሽነር አለሙ መግራ እና የአስተዳደሩ ከፍተኛ የስራ ኃላፊዎችና ካቢኔ እንዲሁም በርካታ የእግር ኳስ አፍቃሪዎች የተገኙበትም ነበረ።
የድሬዳዋ ከፍተኛ ዲቪዚዮን በመክፈቻ ጨዋታ የተገናኙት መስቀለኛ እና ገንደ አብዲ ቦሮ መካከል በነበረው ጨዋታ በመስቀለኛ 2-1 አሸናፊነት ተጠናቋል።
በዚህም ጨዋታ ጥሩ እንቅስቃሴ ያደረገው የመስቀለኛው ካፒቴን ዘመኑ ታረቀኝ የጨዋታው ምርጥ በመባል ተመርጧል::የ5ሊትር ዘይት እና 25 ኪሎ ሩዝ እንዲሁም ማልያ ከነበሩት የክብር እንግዶች ተረክቧል ይህም ሽልማት በየጨዋታው ቀጣይነት እንዳለው ፌዴሬሽኑ ገልፆዋል::