ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ግሩም ጎል ነው ያገባሁት : በጣም ደስ ብሎኛል : ወደፊትም ከዚህ የተሻለ አሳያለሁ ብዬ እጠብቃለሁ “ፍፁም አለሙ

የባህርዳር ከተማው ፍፁም አለሙ የውድድር ዓመቱ ስምንተኛ ጎሉን ዛሬ አስቆጥሮ ቡድኑ የባህርዳር ቆይታውን በቀጣይ ጨዋታዎች በተፎካካሪ ቡድኖች የውጤት ለውጥ ከሌለ ምናልባትም ቡድኑ በሶስተኝነት እንዲያጠናቅም የዛሬዋ ጎል ምክንያትም ሊሆነ ይችላል። የባህርዳር ከተማው አማካይ ፍፁም አለሙ ከጨዋታው በኃላ ከሱፐር ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጎል።በቅድሚያ በርካታ የጎል ዕድሎች በታዮበት ጨዋታ ባንተ ጎል ቡድኑ አሸናፊ በመሆኑ ምን ተሰማህ ለሚለው ጥያቄ ፍፁም ምላሹን በመሥጠት ይጀመራል ” የተለመደ ነገር ስለሆነ ደስተኛ ተሰምቶኛል። ከዚህ የበለጠ ብዙ ጎሎች አግብተን መውጣት የምንችልበት ጨዋታ ነበረ። እግዚአብሔር የፈቀደው እሷን ብቻ ስለሆነ በሷ ጎል አሸንፈናል” በማለት ተናግሯል። ዛሬ ከተቆጠሩት ድንቅ ጎሎች ያንተም ጎል አንዷ ከመሆኗ አንፃር ጎሉን ሃስበኸው ነበር ያገባኸው ለሚለው ጥያቄ ፍፁም አለሙ ሲመልስ ” አዎ…ልመታ ስል ቀጥ ብዬ የበረኛውን አቋቋም አይቼዋለሁ። እናም ግሩም ጎል ነው ያገባሁት። በጣም ደስ ብሎኛል ” ብሏልበቡድኑ ኮከብ ጎል ውስጥ የዳሚ ጎል አስቆጠሪ ከመሆኑ አንፃር በቀጣይ ስለሚያስበው ነገር ተጠይቆ ሲመልስ ” ያው እኔ አማካኝ ስለሆንኩኝ ጎል የመፍጠር ነው ዋና ተግባሬ።ሆኖም ግን እያገባሁ ነው። ቡድኑ በሚፈጥራቸው የጎል ዕድሎች እየሰራሁ ነው። ወደፊትም ከዚህ በተሻለ ነገር አሳያለሁ ብዬ እጠብቃለሁ።” በሚል ገልጿል።ከባህርዳር ከተማ ጋር ቀጣይ ሃሳቡ ለተጠየቀው ፍፁም ሲናገር” እግዚአብሔር ከፈቀደ አሁንም ፉክክር ውስጥ ነው ያለነው። ጠንክረን ከሰራን የማይደረስበት ነገር የለም። ስለዚህ ከፊታችን ያሉትን ጨዋታዎች ልክ ለፍፃሜ እንደምንጫወት አድርገን ካሰብን የማንደርስበት ምንም ምክንያት የለም ብዬ አስባለሁ” ብሏልበመጨረሻም ዛሬ ያስቆጠራትን ጎል ለማን ይሁን ለሚለው ጥያቄ ፍፁም በፈገግታ ተሞልቶ ” ለልጄ ስጦታ ይሁንልኝ ” በሚል ፍፁም አለሙ ከጨዋታው በኃላ ለሱፐር ስፖርት ምላሹን ሰጥቶታል።