ዜናዎች

ጋና ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገው ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ መደረጉን በመቃወም የስታዲየም ለውጥ ጠየቀች !

የጋና እግር ኳስ ማህበር በአለም ዋንጫ ማጣሪያ ከኢትዮጵያ ጋር የሚያደርጉት ጨዋታ በባህርዳር ስታዲየም ዕገዳ ምክንያት  ወደ ደቡብ አፍሪካ መደረጉን በመቃወም በይፋ የተቋሞ ድምፁን አሰምቷል ። 
የጋና እግር ኳስ ማህበር ባለፈው ዓርብ  ለካፍ  እና ለፊፋ በላከው ደብዳቤ በ2022 የአለም ዋንጫ ማጣርያ  ከደቡብ አፍሪካ በ1 ነጥብ ልዩነት  በሁለተኝነት ደረጃ በሚገኝበት አገር ላይ መደረጉ ስህተት ነው በማለት የጨዋታውን ቦታ በፍጥነት እንዲለወጥ  ጥያቄ አቅርቧል።
የጋና እግር ኳስ ማህበር የአለም ዋንጫ ጨዋታዎች ስፖርታዊ ጨዋነት መጓደል እንደሌለበት እና በቀሪዎቹ ሁለት የምድብ ጨዋታዎች ፍትሃዊነት እንዲሰፍን መድረግ እንዳለበት ለፊፋ አመልክቷል።

One thought on “ጋና ከኢትዮጵያ ጋር የሚደረገው ጨዋታ በደቡብ አፍሪካ መደረጉን በመቃወም የስታዲየም ለውጥ ጠየቀች !

Comments are closed.