በአቢጃን ትላንት የተደረገውን የኮትዲቯር ብሔራዊ ቡድን ከኢትዮጵያ አቻቸው ያደረጉትን የአፍሪካ ዋንጫ የመጨረሻ ጨዋታ በመሀል ዳኝነት የመሩት የጋናዊው ዳኛ ቻርለስ ቡሉ በ81ኛው ደቂቃ ባጋጠማቸው ድንገተኛ ህመም ወደ ሆስፒታል መወሰዳቸው ይታወሳል።የትላንቱ የኮትዲቯር እና የኢትዮጵያ ጨዋታ ሊጀመር 3 ሰዓት ሲቀረው የእለቱ ዋና ዳኛ ጋናዊው ዳንኤል በኮቪድ መያዛቸውን ተከትሎ የጨዋታው ኮሚሽነር ከካፍ ጋር በመነጋገር 4ኛ ዳኛው ጨዋታውን የመምራት ሚና ሲሰጠው፤ ጨዋታው ያለ 4ኛ ዳኛ እንዲጀመር የጨዋታው አስተባባሪ እና የጨዋታው ኮሚሽነር መወሰኑ ከጨዋታው በኃላ ተገልጿል።
ጨዋታው በ31 ዲግሪ ሴሊሽየስ እና ከባድ የአየር ሁኔታ የተካሄደ ሲሆን፤ የውሃ እረፍት እንዲሰጣቸው በተደጋጋሚ ተጨዋቾ ቢጠይቁም በውድድሩ በካፍ የተመደቡት ዶክተር እምቢታን በመምረጣቸው ችግሩ ተከስቷል።ሆኖም በ 81ኛው ደቂቃ ላይ ጨዋታውን ሲመሩ የነበሩት ዳኛ በነበረው የአየር ሁኔታ ተዝለፍልፈው በመውደቃቸው ወደ ሆስፒታል ሲወሰዱ፤ ጨዋታው ያለ 4ኛ ዳኛ ሲመራ ስለነበር ጨዋታው 81ኛው ደቂቃ ላይ ተቋርጧል። በኃላም ለ11 ደቂቃዎች የተቋረጠው ጨዋታ ቀጥሎ በኮትዲቯር 3 ለ 1 አሸናፊነት ተጠናቋል። ከአቢጃን በተገኘው መረጃ ጋናዊው ዳኛ ቻርለስ ቡሉ በአሁኑ ሰዓት በጥሩ ጤንነት ላይ እንደሚገኙ ታውቋል።