ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

ጉዳት ያጋጠመው ታሪክ በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል !

በ15ኛ ሳምንት የረፋዱ ወላይታ ድቻ ከአዳማ ከተማ ባደረጉት የሁለተኛ ዙር የመጨረሻ የጨዋታ የቀድሞ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ግብ ጣቢቂ እና ዘንድሮ አዳማ ከተማን የተቀላቀለው ታሪክ ጌትነት በ63ኛው ደቂቃ አስደንቃጭ ግጭት ማስተናገዱ ይታወሳል።የአዳማው ግብ ጠባቂ ታሪክ ጌትነት አስደንጋጩ ጉዳት የደረሠበት በ63ኛው ደቂቃ ላይ ከቡድኑ ተከላካይ አሚን ጋር ሲሆን ግጭቱን ካስተናገደ በኃላ እራሱን ስቶ መተንፈስ አቅቶት የነበረ ሲሆን በቅርበት የነበረው የአዳማው አጥቂ በላይ ዓባይነህ በአጅ እንዲሁም ሌላኛው የአዳማ ተጨዋቾች ፈጣን እርዳታ አድርገዋል። ለኢትዮኪክ በላን መረጃ የአዳማው ግብ ጠበቂ ታሪክ ጌትነት በመልካም ጤንነት ላይ ይገኛል።