- ያሬድ ባዬ (ፋሲል ከነማ) ©
ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

” ይሄን ውጤት ይዘን በደጋፊ ፊት ቢሆን ደስ ይል ነበረ፤ ግን ደግሞ ዋንጫውን ይዘን ስለምንሄድ ቁጭት የለብኝም” – ያሬድ ባዬ (ፋሲል ከነማ) ©

ፋሲል ከነማ የ20 13 የቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ – ሻምፒዮና !
የዐዔዎቹ አምበል ያሬድ ባዬ የ2013 የሻምፒዮናነት ዋንጫን በመጀመሪያ በክብር ከፍ ያደረገው ነው ።ያሬድ ከዛሬው የዋንጫ ማንሳት ስነስርዓት በፊት ለሱፐር ስፓርት ጋር አጭር ቆይታ አድርጓል።
ደጋፊዎች ባሉበት ለመጀመሪያ ጊዜ ጨዋታ ማድረጉ የሚፈጥረው ስሜት ?
” በጣም ደስታን ይፈጥራል። ማለት ከዚህ በፊት ያደረግናቸው ጨዋታዎች ጉልበት አላገኘም ከደጋፊ እና አሁን እንደሚታየው ነው ደጋፊ እና ትንሽም ቢሆን ብርታት ነበሩን ብዬ አስባለሁ”
በፋሲለ ደስ ስታዲየም ጨዋታዎች እና ተመልካች ቢኖሩ ብሎ ተቆጭቶ ከነበረ ?
” ይሄን ውጤት ይዘን በደጋፊ ፊት ቢሆን ደስ ይል ነበረ። ግን ዋንጫውን ይዘን ስለምንሄድ ቁጭት የለብኝም”
በውድድር ዓመቱ ፈታኝ እና ከባዱ ጨዋታ ?
” ከቅዱስ ጊዮርጊስ ጋር የተጫወትነው ጨዋታ ፣ ከሲዳማ ቡና ጋር የተጫወትነው ጨዋታ እና ከቡና ጋር የተጫወትነው ሶስቱ ጨዋታዎች “
በውድድር ዓመቱ አሽቸጋሪ አጥቂ ለእሱ የነበረው ?
” የእኛ እንደ ቡድን ነው የምንከላከለው እና አስቸገረን ብዬ የማስበው እዚህ ሜዳ የተጫወትነው የሲዳማ ቡና ቡድን አጥቂዎቹ ትንሽ አስቸጋሪ ነበሩ”
በልጅነቱ ተጨዋች ለመሆን ሲያስብ በአምበልነት ዋንጫ አነሳለሁ ብሎ አስቦ እንሚያውቅ ?
” አይ….አምበልም እሆናለሁ ብዬ አስቤም አላውቅም። ያው ፈጣሪ ሲፈቅደው ነው ( በፈገግታ)…..”