ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች የጨዋታ ሪፖርት

” ያስቆጠርኳቸው ጎሎች ለአድዋ መታሰቢያ ይሁንልኝ” አቡበከር ናስር

በአድዋ የድል ቀን በተካሄዱት የ14ኛ ሳምንት የመጨረሻ የቤትኪንግ ሁለት ጨዋታዎች ኢትዮዽያ ቡና ወልቂጤ ከተማን አቡበከር ናስር ሁለት ጎሎች አሸንፏል።ኢትዮጵያ ቡናው ድንቅ አጥቂ በአቡበከር ናስርም በቅዱስ ጊዮርጊሱ ጌታነህ ከበደ 2009 ዓ.ም በ25 ጎል የተያዘውን ሪከርድ ለመስበር ተቃርቧል። በ 19 ጎሎቸ ሊጉን የጎል ደረጃ እየመራ የሚገኘው የኢትዮጵያ ቡናው ድንቅ አጥቂ በአቡበከር ናስር ከጨዋታው በኋላ ከስፖርት ስፖርት ጋር ቆይታ አድርጓል።በቅድሚያ የዛሬውን ጨዋታ አስመልክቶ የተጠየቀውን በመግለፅ ይጀመራል ” ዛሬ ከባድ ጨዋታ ነበር። እነሱም በጣም የተፎካከሩበት እኛ ደግሞ የራቁን ቡድኖች ለመቅረብ እንዲሁም ለቀጣይኝ ለሻምፒዮንነት ነውና የምንጫወተውና ትንሽ ጠንካራ ጨዋታ ነበር” በሚል መልሷልበቤትኪንግ ፕሪምየር ቀድሞ ዮርዳኖስ አባይ በⷛላም በጌታነህ የተያዘውን የጎል ሪከርድ ለመስበር አሁን ላይ እያሰበ ስላለው ተጠይቆ አቡበከር ሲመልስ” የማስበው ሁሌ በማገኘው እና በተሻለ አጋጣሚ ጎል ማስቆጠር ነው። የጎል ሪከርዱን ደግሞ ለቀጣይም ከእነሱ በላይም ማግባት ነው ዓላማዬ እናም በዚህ አመት የተሻለ ነገር አመጣለሁ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ” በማለት ይናገራል ። በኢትዮዽያ ፕሪምየር ሊግ ከ16 አመት በፊት የሪከርዱ ባለቤት ከነበረው ከዮርዳኖስ አባይ ጋር መገናኘቱንና ማውራታቸውን አስመልክቶ ለጠየቀው ሲመልስ ” አዎ ዮርዳኖስ ደውሎልኝ አውርተናል። በጣም ነው ደስ ያለኝ ። ምክንያቱም ስለ እሱ በጣም ነበር የምሰማው ። ብዙም ሲጫወት አላየሁትም እና ደውሎ ሲያወራኝ በጣም ደስ ብሎኝ ደንግጬም ነበረ በደስታ። በርታ ስላለኝም በዚህ አጋጣሚ አመሠግናለሁ” ብሏል የአድዋ ድል ክብረ በዓልን አስመልክቶ የሚያስተላልፈው መልዕክት ካለ ተጠይቆ ” ያስቆጠርኳቸው ጎሎች ለአድዋ መታሰቢያ ይሁንልኝ” ብሏል የኢትዮጵያ ቡናው ድንቅ አጥቂ በአቡበከር ናስር