ዜናዎች

የ2014 የፕሪሚየር ሊግ ተሳታፊ 6 ክለቦችን ለመለየት ዛሬ ዕጣ ማውጣት ይደረጋል !-የመጀመሪያ ቡድን ባህርዳር ደርሷል

የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን የስራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ሰኔ 1/2013 ዓ.ም አስተላልፎት በነበረው አስቸኳይ ስብሰባ በ2ኛ አማራጭ የትግራይ ክልል ክለቦች ፕሪሚየር ሊጉ ከአቅም በላይ በሆነ ምክንያት የማይመዘገቡ ከሆነ በሚል በአማራጭ ያዘጋጀው የጥሎ ማለፍ ውድድር የፊታችን ሰኔ 18/2013 ዓ.ም በሐዋሳ ከተማ መካሄድ ይጀምራል። ስድስት ቡድኖች የሚሳተፉበት ውድድር የዕጣ ማውጣት ስነስርዓት ዛሬ  ይካሄዳል። በ2013  የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በሊጉ ደረጃ ግርጌ የሚገኙት ወራጅ ክለቦች ጅማ አባጅፋር ፣ወልቂጤ ከተማ እና አዳማ ከተማ  ከከፍተኛ ሊግ በሦስት ምድቦች ሁለተኛ የወጡት ኮልፌ ቀራኒዮ ክ/ከ፣ ሀምበሪቾ ዱራሜ እና ኢትዮ ኤሌክትሪክ ጋር ተጫውተው  በነጥብ ውድድር ተሳትፈው ከ1-3 ከወጡት ክለቦች መካከል የተሻለ ነጥብ ያስመዘገበው በቅደም ተከተል በፕሪሚየር ሊጉ እንዲሳተፍ ይደረጋል።