የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ውድድር አመራርና ስነ-ስርዓት ኮሚቴ ሰኞ መስከረም 28 2016 ዓ.ም ባደረገው ስብሰባ የተደረጉ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ ግጥሚያ(ዎች)ከዳኞች እና ከታዛቢዎች የቀረቡለትን የዲሲፕሊን ሪፖርት ከመረመረ በኋላ የተለያዩ ውሳኔዎች አሳልፏል።
በተጫዋች ደረጃ በረከት ሳሙኤል (ሃዋሳ ከተማ) ክለቡ ከ ፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ ላይ ሁለተኛ ቢጫ ካርድ የሚያስጥ ጥፋት በመፈፀሙ ቀይ ካርድ አይቶ ከጨዋታ ሜዳ የተወገደ ለፈፀመው ጥፋት በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት 1 ጨዋታ እንዲታገድ ሲወሰን አቶ ሸምሰዲን ከድር /ሻሸመኔ ከተማ-የቡድን መሪ / ክለቡ ከ ከወላይታ ድቻ ጋር በነበረው ጨዋታ ቅድመ ስብሰባ ወቅት ዘግይተው በመምጣታችው ለፈፀሙት ጥፋት በፕሪምየር ሊግ የውድድር ደንብ መሰረት ብር 1000/አንድ ሺ ብር/ እንዲክፍሉ ተወስኗል።
በክለብ ደረጃ ሃዋሳ ከተማ ክለቡ ከፋሲል ከነማ ጋር ባደረገው ጨዋታ የሃዋሳ ከተማ ቡድን አምስት ተጫዋች በተለያዩ ጥፋቶች ካርድ የተሰጣቸው በመሆኑ በኢ.እ.ፌ ዲሲፕሊን መመሪያ መሰረት የገንዘብ ቅጣት ብር 5000 /አምስት ሺ/ እንዲከፍል ተወስኗል፡፡