ዜናዎች

የጋና እና የኢትዮጵያ የምሽቱ ጨዋታ በጋና አሸናፊነት ተጠናቋል!

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በጋና አስተናጋጅነት  ዛሬ በተጀመረው በ13ኛው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ውድድር ላይ   ዛሬ ምሽቱን  የምድቡን የመጀመሪያውን ጨዋታውን አድርጎ ተሸንፏል።

በአሰልጣኝ ዮሴፍ ገ/ወልድ እየተመራ  ወደ ጋና ያቀናው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከ 11 ቀሚ ተሰላፊዎች ጋራ አራት ተቀያሪ ተጨዋቾች  ብቻ ይዞ ነው  የተጓዘው።
የጋና እና የኢትዮጵያ  ቡድኖች በምሽቱ ጨዋታ  ላይ መብራት በኬፕ ኮስት ስታዲየም  በመጥፋቱ  ለ20 ደቂቃዎች  ጨዋታው ተቆርጦ የነበረ ሲሆን የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን በጋና ባደረገው  የምድቡ  የመጀመሪያውን ጨዋታውን 1 ለ 0 ተሸንፈዋል።