ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች

#የድሬዳዋ ከንቲባ – መልካም ተግባር

አንጋፋው ኢንተርናሽናል ዳኛና የጨዋታው ኮሚሽነር ይድነቃቸው ዘውገ(ቦቼ) በደረሰበት የጤና ችግር ሀገር ውስጥ መታከም ባለመቻሉና ወደ ውጪ ሀገር ሄዶ እንዲታከም በሐኪሞች መወሰኑ እና የስፖርት ቤተሰቡን ድጋፍ መጠየቁ ይታወሳል።
በዚህ መሠረት የድሬዳዋ አስተዳደር ከንቲባ ከድር ጁሃር በዛሬው ዕለት በአንጋፋው ኢንተርናሽናል ዳኛ ይድነቃቸው ዘውገ መኖሪያ ቤቱ ተገኝተው ጠይቀውታል፡፡ በኩላሊት ህመም ላይ የሚገኝው ይድነቃቸው ዘውገ /ቦቼ / ክቡር ከንቲባው ለህክምናው 5 መቶ ሺህ ብር ( 500,000) የገንዘብ ድጋፍ አድርገዋል::
ለመርዳት ለምትፈልጉ
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁ. 1000500798339
ስልክ ቁጥር 0915734423 / 0911668719