
ዛሬ ረፋድ የወላይታ ድቻው አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከስፖርት ዞን አዘጋጅ ሰኢድ ኪያር ጋር ባደረጉት ቆይታ እንደተናገሩት የኮቪድ ምርመራ ጋር እያጋጠማቸው ያለውን ከፍተኛ ችግርም በስፋት አንስተውም አሰልጣኙ ተናግረዋል። በተለይም ኮቪድ ምርመራው ውጤት ከሁለት የጤና ተቋማት የተለያዩ መሆን በክለቦች ላይ ትልቅ ተፅኖ እንዳለው ገልጿል። እንደምሳሌም በቡድናቸው ባጋጣሚ ያልተመረመሩ ተጨዋቾች ጨምሮ አለማያ ዩኒቨርስቲ ኮቪድ አለባችሁ እንደተባሉ ተናግሯል። አሰልጣኝ ዘላለም እንዳለው አወዳዳሪው አካል ዘላቂ መፍትሔ እንዲፈልግም አሳስቧል።
ወላይታ ድቻ ዛሬ ከሰበታ ከተማ በሚያደርገው ጨዋታ ዋና አሰልጣኝ ዘላለም ሽፈራው ከኮቪድ ጋር በተያያዘ በጨዋታ ሜዳ የማይገኝ ሲሆን በሜዳ ላይ ቡድኑን ይዞ የሚገባው ምክትል አሰልጣኝ ዳዊት ሀብታሙ እንደሚሆን ይጠበቃል።