ቤትኪንግ ፕሪሜር ሊግ ዜናዎች የ2013 ሊጎች እና ውድድሮች

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አ.ማ የቦርድ አመራር ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ በቀጣይ ውድድሩ ላይ ውሳኔ አስተላልፏል።

 

ቤትኪንግ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ 2015 የ12ኛ እና የ11ኛ ሳምንት ተስተካካይ ጨዋታዎች እንዲሁም ከ14ኛ ሳምንት በኋላ ያሉ ጨዋታዎችን መካሄጃ ከተማና ስታዲየም በተመለከተ የስራ አመራር ቦርዱ ዛሬ ጥር 28/2015 ዓ.ም ባደረገው አስቸኳይ ስብሰባ የተለያዩ ውሳኔዎችን አስተላልፏል።

በዚህም መሰረት ውድድሩን በድሬደዋ ወይም ባህር ዳር ከተማ ለማከናወን የፊታችን ሰኞ ጥር 29/2015 ዓ.ም ሜዳዎቹን የሚገመግም ኮሚቴ(ከቦርዱ እና ውድድርና ስነስርዓት ኮሚቴ) ለመላክ ፤ ማክሰኞ ጥር 30/2015 ከሁለቱ የተመረጠውን ሜዳ በተመለከተ ውሳኔ ለማስተላለፍ ሲሆን የሊግ ውድድሩ የፊታችን ቅዳሜ የካቲት 04/2015 የሚጀምር መሆኑን አሳውቋል።

የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ አክስዮን ማህበር ስራ አመራር ቦርድ