ዜናዎች

የኢትዮጵያ ከ23 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በባህር ዳር ዝግጅቱን አጠናክሮ ቀጥሏል!

በኢትዮጵያ አስተናጋጅነት በባህር ዳር ከተማ ከሰኔ 26 እስከ ሐምሌ 11 ቀን 2013 ዓ.ም የሚካሄደው የሴካፋ ከ23 ዓመት በታች የወንዶች እግር ኳስ ዋንጫ ውድድር 11 የሴካፋ አባል ሀገራትን እና ተጋባዧ ዲሞክራቲክ ሪፕብሊክ ኮንጎን ያሳተፈ ነው።
በዚሁ ውድድር ኢትዮጵያን የወከለው ከ23 ዓመት በታች የተስፋ ቡድን በአሰልጣኝ ውበቱ አባተ እየተመራ ሐሙስ ሰኔ 17 ቀን 2013 ዓ.ም ባህር ዳር በመግባት ልምምዱን አጠናክሮ ቀጥሏል።ቡድኑ ባህር ዳር ከተማ እንደደረሰ በክልሉ የተቋቋመው የሴካፋ የውድድር ኮሚቴ ደማቅ አቀባበል አድርጎለታል
@መረጃ የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን