ዜናዎች

የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች የሴቶች ብሔራዊ ቡድን ጅቡቲን 7 ለ 0 አሸነፈ!

የኢትዮጵያ ሴቶች ከ20 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን በዩጋንዳ አስተናጋጅነት ከጥቅምት 20 – እስከ ጥቅምት 30/2014 ለሚካሄደው የምሥራቅና
የሴካፋ ውድድር ዛሬ የመጀመሪያ ጨዋታውን
በድል ጀምሯል።

በዮጋንዳ አስተናጋጅነት በሚካሄደው የሴካፋ የታዳጊዎች ውድድር ኢትዮጵያ ጅቡቲን 7 ለ 0 አሸንፋለች። ጎሎቹን ረድኤት አስረሳኸኝ ሶስት ጎሎች አስቆጥራ ሐትሪክ ስትሰራ ፣ ቱሪስት ለማ ሁለት ጎሎች
እፀገነት ግርማ እና ቤተልሔም በቀለ አንድ ጎሎች አስቆጥረዋል።