የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የኤፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን ጋር በመሆን የኢትዮጵያ ብሔራዊ የወንዶች እግርኳስ ቡድን ወደ ካሜሩኑ የአፍሪካ ዋንጫ ማለፋቸውን ተከትሎ የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የ6 ሚሊዮን ብር እና የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን ከ8 ሚሊዮን ብር ሽልማት እና 3 ሚሊዮን ብር ለፕሮግራሙ ወጪ የተደረገ ሲሆን በአጠቃላይ የተለያዩ ወጪዎችን ጨምሮ የኢፊድሪ ስፖርት ኮሚሽን 10 ሚሊዮን ብር አበርክቷል ።
የኤፌድሪ ስፖርት ኮሚሽን የሽልማቱ ዝርዝር
1. ለዋና አሠልጣኝ 350ሺ
2. ለ3ቱ ረዳት አሠልጣኞች ለእያንዳንዳቸው 250 ሺ
3. ለ18 ቋሚ ተሰላፊዎች ለእያንዳንዳቸው 250 ሺ
4. ለ5ተቀያሪ ተጨዋቾች ለእያንዳንዳቸው 150 ሺ
5. ለ6 ኮችንግ ስታፍ አባላት ለእያንዳንዳቸው 100 ሺ
6. ለትጥቅ ያዥ 75 ሺ
7. ለቡድን መሪ እና ቴክኒክ ዳይሬክተር 150 ሺ
8. ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት 100 ሺ ብር
እንዲሁም ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለእያንዳንዳቸው 75 ሺ ብር ማበረታቻ ተደርጎላቸዋል ።
የፌዴሬሽኑ የስድስት ሚሊዮን ብር ለቡድኑ አጠቃላይ አባላት ሽልማት ዝረዝር
1. ለዋና አሠልጣኝ 300 ሺ
2. ለ3ቱ ረዳት አሠልጣኞች ለእያንዳንዳቸው 150 ሺ
3. ለተጫዋቾች ለእያንዳንዳቸው 140 ሺ
4.ለቡድን መሪው አቶ ባህሩ ጥላሁን 150 ሺህ
5. ለህክምና ባለሙያዎች ለእያንዳንዳቸው 70 ሺ
6. ለትጥቅ ያዥ 75 ሺ
7. ለቡድን መሪ እና ቴክኒክ ዳይሬክተር 70 ሺ
8. ለኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌዴሬሽን ፕሬዚዳንት 100 ሺ ብር
እንዲሁም ለስራ አስፈፃሚ ኮሚቴ አባላት ለእያንዳንዳቸው 75 ሺ ብር ማበረታቻ ተደርጎላቸዋል ።
Very good