ዜናዎች

የአይቮሪኮስት አና የኢትዮጵያን ጨዋታ ጋናዊው የመሀል ዳኛ ይኖሩታል !

በካሜሩን አስተናጋጅነት ለሚካሄደው የአፍሪካ ዋንጫ ለማለፍ የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ከአይቮሪኮስት አቻቸው ጋር የመጨረሻውን የማጣሪያ ጨዋታው የፊታችን ማክሰኞ ያካሂዳል። ይህንን ጨዋታ ጋናዊው ኢንተርሽናል አርቢትር ዳንኤል አዬ ላሪያ ይመሩታል። የሁለቱ ቡድኖች ተጠባቂውን ጨዋታውም 60,000 ተመልካች የመያዝ አቅም ባለውና እግር ኳስ ፣ ራግቢ እና አትሌቲክስ በሚያስተናግደው በስታድ ዲ ኤቢምፔ ሁለገብ ስታዲየም ይደረጋል። ጨዋታውን ክጋናዊው ኢንተርሽናል በዋና ዳኝነት ዳንኤል በተጨማሪ በረዳት ዳኝነት ኬኒያዊው ጊልበርት ኪፕኮች ሲሆን ጋናውያኑ ክዋሲ አቼምፓንግ እና ቻርለስ ቤን በቅደም ተከተል 2 ኛ ረዳት እና 4 ኛ ዳኛ መሆናቸው ታውቋል።እንደሚታወሰው ትላንት ማለፉን ያረጋገጠው አይቮሪኮስት ከኢትዮዽያ ጋር ባደረገው የመጀመሪያው ጨዋታ 2 ለ 1 በባህርዳር መሸነፉ ይታወሳል።