ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር ከክለቡ ማሜሎዲ ሰንዳውንስ ጋር የደቡብ አፍሪካ ፕሪሚየር ሊግ (PSL) ሻምፒዮን ከሆነ በኃላ ለዕረፍት አቡበከር በኢትዮጵያ ይገኛል።
የዋልያዎቹና የሰንዳውንስ የፊት መስመር አጥቂ አቡበከር ናስር የደቡብ አፍሪካ ቆይታው ለወራቶች በጉዳት የነበረ ቢሆንም በተሰለፈባቸው ጨዋታዎች ለቡድኑ ጠቃሚ ተጨዋች መሆኑንም አሳይቷል።
ኢትዮጵያዊው የማሜሎዲ ሰንዳውንስ የፊት መስመር ተጨዋች አቡበከር ናስር አሁን ላይ በኢትዮጵያ መገኘቱን ተከትሎ በርካቶች ለምን ትላንት ይፋ በሆነው የኢትዮዽያ ብሔራዊ ቡድን ስብስብ አልተካተተም የሚል ጥያቄዎች ማንሳታቸው የሚጠበቅ ነው።
ሆኖም መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ተጨዋቹ አሁን ያለበት ሁኔታ ለጨዋታ ዝግጁ የሚያደርገው ስላልሆነ ከአሰልጣኞቹ ጋር ከተወያየ በኋላ በብሔራዊ ቡድኑ ስብስብ ሳይካተት መቅረቱ ታውቋል።
አቡበከር በአሁኑ ወቅት ከቁርጭምጭሚት ጉዳት ሙሉ ለሙሉ ባለማገገሙ እና ከጉዳቱ በፍጥነት ያገግም ዘንድ ከክለቡ የተሰጠውን የማገገሚያ ልምምድ እየሰራ መሆኑን አስረድቶ በቡድኑ ውስጥ አሁን ላይ አለመካተቱን ስፖርት 24 ዘግቧል።
🙏🙏🙏🙏