የፋሲል ከነማ አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ትላንት ቡድናቸው የሊጉን ዋንጫ ግስጋሴውን ያቀናበትን ሶስት ነጥብ ይዞ ከወጣ በኋላ ተጨዋቾቹ በደስታ ሲዘምሩ እሳቸው በደስታ ሲያነቡ ተስተውሏል። የ19ኛው ሳምንት የሊጉ ጨዋታ ፋሲል ከነማ ሲዳማ ቡናን 2 ለ1 ካሸነፈ በኃላ በመልበሻ ቤት አሰልጣኝ ስዪም ከበደ እጅጉን ስቅስቅ ብለው አልቅሰዋል።
የዓፄዎቹ ዋና አሰልጣኝ ስዪም ከበደ ለቅሷቸው የደስታ ቢሆንም አብሮ የተያያዘ ነገር ስለመኖሩ ኢትዮኪክ ጠይቀናቸው አሰልጣኝ ስዩም የሚከተለውን ይላሉ ” እንደሚታወቀው እግር ኳስ እና ሙያው በፈተና እና በፈተና የተከበበ ነው። ስታልፈው ስሜቱ ጥልቅ ነው፡፡ እንደሚታቀው በፋሲል ከነማ በቡድኑ ውስጥ ደጋፊ የሚመስሉ አንዳንድ ተራ የሆኑ ሰዎች ስራዬን ለማሰናከል ሞክረው ነበር። እነዚህ የቡድኑ ፀር የሆኑ ሰዎች ስናሸነፍም ስድብ ነው ፣ ቡድኑ ሲሸነፍም እንደዛው ናቸው። እግዚአብሔርይመስገነው ። እሱን ሁሉ አልፌ ከልጆቼ ጋር አሁን ሻምፒዮና መንገድ ላይ ሆነን ነው ። የትላንቱ የደስታ ስሜት ጥልቅ ነው ። ለእግር ኳስ ሙያው አብራኝ ስትጨነቅ የነበረችው እናቴ በህይወት ኖራ አሁን በስኬት ጎዳና ላይ ደስታዬን ብታይልኝል እሱም ደስ ይለኝ ነበር። እናም የትላንቱ ለቆሶ በብዙ የደስታ ስሜቶች የተቀላቀለበት ነው ። እንዳልኩት እግዚአብሔር ይመስገነው ፣የትላንቱ የለቆሶው ስሜት ያለፍኩበትን የትግል ወራቶች ያስታወሰ ስሜት ነበር ማለት እችላለሁ ” በማለት አሰልጣኝ ስዪም ከበደ ለኢትዮ ኪክ ተናግረዋል።
የዓፄዎቹ ዋና አሰልጣኝ ስዩም ከበደ ደስታቸውን በማልቀስ የገለፁበት ቪዲዮ