በ2016 ዓ.ም ክለቦች በፕሪሚየር ሊጉ የተሻለ ሆነው ለመቅረብ የሚፈልጓቸውን ተጨዋቾች የዝውውር ሂዱቱ በይፋ ማጧጧፍ እና በተጨዋቾች ደላሎች በኩል የማግባባት ስራዎች ቀጥለዋል።
በተጨዋቾች ዝውውር ሂደት ከስምምነት የደረሱት በይፋም የተሳካለቸው በተለያዩ መረጃ ምንጮ ይፋ እንደሆኑ ሁሉ ስማቸው እየተነሱ ከሚገኙ በርካታ ተጨዋቾች ጥቂቶቹን በቀጣይ ቀናት ለእናንተ እናደርሳለን። በተለይም በተጨዋቾች የድርድር ሂደት ለቀጣይ ዓመት ከፍተኛ ብር በመወጣት ለማስፈረም ክለቦች የማግባት ሂደቱን መቀጠላቸው እጅጉን ትኩረት የሰጡ ናቸው ። አንዳንዶቹ ክለቦች በከተማና በክልል በጀት የሚተዳደሩ ከመሆኑ አንፃር ደግሞ ለአንድ ተጨዋች ከፍተኛ ክፍያ አድርገው ለማስፈረም የሚያደርጉት ጥረት ትኩረቱን የበለጠ አነጋጋሪ ሲያደርገው እነዚሁ ክለቦች በዓመቱ አጋማሽ በገንዘብ እጥረት ለቡድኑ አባለት የወር ክፍያ አቅም ማጠር ሊያጋጥማቸው እንደሚችል የዘንድሮውን ጨምሮ ካለፉት ዓመታት ልምዶች አንፃር ቀድሞ መገመት ይቻላል።
በዚህ ዝውውር ሂደት በተለይ ደግሞ አንድ ተጨዋች በ13 ሚሊዮን ለማስፈረም የሚደረገው ሙከራ እጅግ አነጋጋሪ መሆኑን ቀጥሏል።
🔛በይፋ የፈረሙ ተጨዋቾች
🔛⭕ ቀድሞ ባሉት ዓመታት በሙገር በመቻል ፣ በሃዋሳ እና በ2015 በሲዳማ ቡና ክለብ ደግሞ የውድድር ዓመቱን 30 ጨዋታዎች የተጫወተው ፍሬዉ ሰለሞን በ2016 በባህርዳር ከተማ ለመጫወት በሁለት አመት ውሉን አኑሯል ።
🔛⭕ ያለፉትን ዓመታት በደደቢት ፣ሰበታ ከተማና የወላይታ ዲቻ የመስመር አጥቂው የነበረው ቃልኪዳን ዘላለም የዓፄዎቹ የመጀመሪያ ፈራሚ ሆኗል።
🔜 በቀጣይ ቀናት የሚፈርሙ
🔜⭕ የወላይታ ዲቻ የመስመር ተመላላሽ ያሬድ ዳዊት ከወላይታ ዲቻ የሚኖረው ቆይታ ያበቃ ይመስላል። ተጨዋቹ በሊጉ ከሚገኙ ሌሎች ክለቦች የተሻለ ክፍያ የሚያቀርቡለት ከሆነ በቀጣይ ቀናን የ2016 ማረፊያ ክለቡ የሚታወቅ ማለት ነው።
🔜⭕ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በተካዱት የሊጉ ጨዋታዎች ሁሉንም የተጫወተው የወላይታ ዲቻው መልካሙ ቦጋለ በቀጣይ ዓመት ኢትዮጵያ መድን ሊቀላቀል ንግግር ላይ እንደሚገኝ ታውቋል።
🔜⭕ በዘንድሮ የውድድር ዓመት ላይ የተጫወቱ እና ለቡድናቸው በጥሩ አቋም ላይ የበርካታ ተጫዋቾች ሰሞኑን ወደ ዉጪ ሊጎች ያመራሉ ፤ ያልተገመቱ ተጫዋቾችም ጭምር ወደ ዉጪ ለማምራት ሂደቶች ላይ መሆናቸው ተሰምቷል። ከነዚህ መዓል የሲዳማ ቡናው ጊት ጋት ኩት ከግብጽ ክለቦች ጋር ስሙ ተነስቷል።
🔛⭕ በ2015 ከሀዲያ ሆሳዕና ክለብ ጥሩ ጊዜን ያሳለፈው ባዬ ገዛኸኝ ወደ ቀድሞ ወላይታ ዲቻ ሊመለስ መሆኑ ተሰምቷል። በጉዳዩ ላይ ኢትዮ-ኪክ ባዬን ከቀናት በፊት ጠይቀነው ለጊዜው ባዬ በጉዳዩ ላይ ምላሽ ከመስጠት ተቆጥቧል።
የኢትዮ ኪክ L (ሊንኮቻችን)
#አዲሱ የቲክቶክ ገፃችን
tiktok.com/@ethiokick
#በቴሌግራም :-
https://t.me/Ethio_Kickoff
#በኢንስታግራም ገጻችንን :-
https://www.instagram.com/ethio_kick
🔛ድረ ገጻችንን :-