
ወንድሜህ ጎል አስቆጥሮ ነበር? የትኛው ያምራል?
በፈገግታ አዎ ጎሉን አይቼዋለሁ። የኔ ጎል ያምራል ብዬ አስባለሁ። (በፈገግታ) አላዳላሁም ….
ከባዬ ጎልና ካንተ ቤተሰብ በየትኛው ይደሰታል?
” መጀመሪያ ያየሁት የሱን ጎል ነው። እንደ ታላቅም ወደ እሱ ጎል የሚያደሉ ይመሥለኛል ቤተሰቦቼ። ወደ እሱ ያደላሉ ብዪ አስባለሁ።
እንደቤተሰብ ተፎካክራችሁ ተውቃላችሁ በጎል አስቆጣሪነት ?
“አምና ተፎካክረን ነበረ። እሱ ሲያገባ እኔም አገባለሁ። እስኪቋረጥ ድረስ ሁለታችንም ዘጠኝ ጎል አግብተን በእኩል ነበር የጨረስነው። እናም ፉክክር ነበር በሁለታችንም መካከል ነበረ ።
ዘንድሮስ ?
” ዘንድሮ እንደ ቡድን አጀማመራችን ጥሩ አልነበረም። ግን አሁን እየተሻሻለ ሲመጣ ወደ ጎል እየቀረብን ነው። ይህንን ለማሻሻል እየሰራን ነው።
ከዛሬ ጨዋታ በፊት ክኮቪድ ጋር በተያያዘ ቡድኑ ስለነበረው በ ጫና ?
” አዎ ከባድ ነበር። አሁን አስቸጋሪ ነው። ኮቪድ ያለበት ወቅቱ አስቸጋሪ ነው ለእኛም ።
ኮቪድ ተይዟል ከተባለው 23 ተጨዋቾች ውስጥ ስለመኖሩ ?
” አዎ ነበርኩኝ። ግን ደግሞ የተባለው የኮቪድ ነገር ትንሸ ውሸት ነው ብዬ ነው የማስበው ። ምክንያቱም እዚህ ከመጣን በኃላ ተመርምን ነበር ያንን አልተቀበልነውም ። ሁላችንም ላይ ትንሽ የእህምሮ ተፅኖ ፈጥሮብናል። ያም ይሁን ብለን ወደ አለማያ ዮኒቨርስቲ በማታ ተጉዘን ተመርምረን ውጤቱ በመቀልበሡ ደስ ብሎናል።
